1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሩዋንዳው እልቂትና አስተምህሮቱ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 9 2006

የጀርመን መንግሥት የሰብዓዊ ጉዳዮች ተጠሪ ክርስቶፍ ሽትሬሰር ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ በተለይ ግጭቶች እየተባባሱ በሚሄዱባቸው አካባቢዎች ህዝቡን በሰብዓዊ እርዳታ መደገፍ ከዚያም አልፎ ተፋላሚ ወገኖችን ቢቻል በሰላማዊ መንገድ አለያም በኋይል ማስቆም እንደሚገባ አሳስበዋል ።

https://p.dw.com/p/1BkOj
Christoph Strässer MdB SPD
ምስል picture-alliance/spdfraktion.de/Susie Knoll/Florian Jänicke

የዛሬ 20 ዓመት በሩዋንዳ የተካሄደው ጭፍጨፋ በአፍሪቃ ዳግም እንዳይከሰት አውሮፓውያን ከወዲሁ የጥንቃቄ እርምጃዎችና ዝግጅቶች ሊያደርጉ እንደሚገባ አንድ የጀርመን መንግሥት ባለሥልጣን አሳሰቡ ። የጀርመን መንግሥት የሰብዓዊ ጉዳዮች ተጠሪ ክርስቶፍ ሽትሬሰር ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ በተለይ ግጭቶች እየተባባሱ በሚሄዱባቸው አካባቢዎች ህዝቡን በሰብዓዊ እርዳታ መደገፍ ከዚያም አልፎ ተፋላሚ ወገኖችን ቢቻል በሰላማዊ መንገድ አለያም በኋይል ማስቆም እንደሚገባ አሳስበዋል ።ይህን የመሰለውን የአፍሪቃ ችግር ለመቋቋም የአውሮፓ ህብረትም ሆነ ጀርመንን የመሳሰሉ የአውሮፓ መንግሥታት ያወጡት እቅድ የለም ሲሉ ባለሥልጣኑ ተችተዋል ። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል ዝርዝሩን ልኮልናል

ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ