1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የምርጫ ቅስቀሳ በደቡብ ክልል

ዓርብ፣ ግንቦት 14 2007

በደቡብ ክልል ቡርጂ የምርጫ ጣቢያ የገዢዉ ፓርቲ ካድሬዎች በመንግሥት ተሽከርካሪ እየቀሰቀሱ ነዉ፤ የምርጫ ፖስተር ናሙናም የኢህአዴግ ምልክት የሆነዉን ንብ ብቻ አድርገዉ ሕዝቡን እያሳሳቱ ነዉ ሲል መድረክ ወቀሰ።

https://p.dw.com/p/1FTsG
Äthiopien Wahlen 2015
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

[No title]

የምርጫ ምልክቶችን የያዘዉ የናሙና ፖስተር በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች አለመለጠፉንም መድረክ አክሎ ገልጿል። የወረዳዉ ምርጫ ቦርድ ጽሕፈት ቤት በበኩሉ የገዢዉ ፓርቲ ካድሬዎች ለመቀስቀስ ሲዘጋጁ ደርሼበት በደብዳቤ እንዲያስቆሙ አድርጌያለሁ፤ የምርጫ ምልክቱን የያዘ ፖስተርም በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ለጥፈናል ብሏል። ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር ከአዲስ አበባ ዝርዝሩን ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ