1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመኢአድ አቤቱታና የምርጫ ቦርድ መልስ

ሰኞ፣ ሚያዝያ 6 2006

የመኢአድ አባላት ከእስር ሌላ በአንዳንድ አካባቢዎች ስብሰባ ማድረግ እንደሚከለከሉና በአጠቃላይ የመደራጀት መብታቸው እንደተነፈገ አመራሮቹ አስታውቋል ። የክልሉ የምርጫ ቦርድ በበኩሉ ሰሞኑን የቀረበ ቅሬታ መኖሩን እንደማያውቅ ከዚያ ቀደም ሲል ግን በፖለቲካ ምክንያት የታሰረ ሰው እንደሌለ አስታውቋል ።

https://p.dw.com/p/1BhrF
12.06.2013 DW Online Karten Basis Äthiopien Englisch

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ በደቡብ ክልል አባላቱ እስር ወከባና ልዩ ልዩ የመብት ጥሰቶች ይፈፀሙባቸዋል ሲል አማረረ የድርጅቱ አመራር አባላት ለዶቼቬለ እንደተናገሩት በአሁኑ ጊዜ በደቡብ ክልል 16 የአመራር አባላት በእሥር ላይ ይገኛሉ በክልሉ የመኢአድ አባላት ከእስር ሌላ በአንዳንድ አካባቢዎች ስብሰባ ማድረግ እንደሚከለከሉና በአጠቃላይ የመደራጀት መብታቸው እንደተነፈገ አመራሮቹ አስታውቋል የክልሉ የምርጫ ቦርድ በበኩሉ የሚደርሱትን አቤቱታዎች አጣርቶና ተከታትሎ ለፌደራል ምርጫ ቦርድ እንደሚያሳውቅ በፍትህ አካላት በተያዙት ጉዳዮች ግን ጣልቃ እንደማይገባ መልስ ሰጥቷል ሆኖም ሰሞኑን የቀረበ ቅሬታ መኖሩን እንደማያውቁ የገለጹት የደቡብ ክልል ምርጫ ቦርድ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሃላፊ ከዚያ ቀደም ሲል ግን በፖለቲካ ምክንያት የታሰረ ሰው እንደሌለ ተናግረዋል

ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ