1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሐይማኖት ዓለሙ ቀብር

ማክሰኞ፣ መስከረም 13 2007

ሐይማኖት አለሙ በተዋኝነት፤በአዘጋጅነትና በፀፌ ተዉኔትነት በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ዉጪ በተለይ ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ በበርካታ ድራማዎች ተሳትፏል። ሐይማኖት በተለያዩ ቲያትሮች በሥራ-አስኪያጅነትና በአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲም በመምሕርነት ያገለገለ የጥበበብ ሰዉ ነበር። 68 ዓመቱ ነበር።

https://p.dw.com/p/1DJIz
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

ኢትዮጵያዊዉ ፀሐፌ ተዉኔት፤አዘጋጅ፤ተዋኝና የቲያትር ጥብብ መምሕር ሐይማኖት ዓለሙ ዛሬ በአዲስ አበባ ቅድስት ሥላሴ ቤተ-ክርስቲያን ተቀበረ። ሐይማኖት አለሙ በተዋኝነት፤በአዘጋጅነትና በፀፌ ተዉኔትነት በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ዉጪ በተለይ ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ በበርካታ ድራማዎች ተሳትፏል።ሐይማኖት በተለያዩ ቲያትሮች በሥራ-አስኪያጅነትና በአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲም በመምሕርነት ያገለገለ የጥበበብ ሰዉ ነበር።68 ዓመቱ ነበር።ያረፈዉ ባለፈዉ እሁድ ነዉ።በቀብሩ ሥነ ሥርዓት ዘመድ-ወዳጆቹ፤ የመንግሥት ባለሥልጣናት እና የሐይማኖት መሪዎች ተገኝተዋል።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚ አብሔር የቀብሩን ሥርዓቱን ተከታትሎት ነበር።

ዮሐንስ ገብረ እግዚ አብሔር

ነጋሽ መሐመድ