1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሐኖቨሩ ዓለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክስ ትርዒት፣

ረቡዕ፣ መጋቢት 3 2006

ባለፈው ዓመት ፣ የዩናይትድ ስቴትስና የብሪታንያ የስለላ ድርጅቶች ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ፣ የድርጅቶችን ፣ የግለሰቦችን የታወቁ የሀገር መሪዎችን የግል ተንቀሳቃሽ ስልኮች የድምጽ፤ የጽሑፍና ስዕል አገልግሎት ጭምር ይጠልፉ ነበር ተብሎ፣ ዜናው በዓለም

https://p.dw.com/p/1BOih
ምስል Deutsche Messe

ዙሪያ ከተዳረሰበት ጊዜ አንስቶ፤ ጉዳዩ ብዙ ሲያነጋግር ቢቆይም፤ የኤልክትሮኒክሱን ምርትና ገበያ አልገታውም። ያም ሆኖ ፣ በተገልጋዮች(ተጠቃሚዎች) ዘንድ የተፈጠረውን የአመኔታ እጦት ለማርገብ ፣ ዘመናዊ የእጅ ስልክ ሠሪ ኩባንያዎችን ሰፊ ጥረት መጠየቁ አይቀሬ ነው። ለዚህም ሳይሆን አልቀረም ፤ በዓለም ውስጥ በግዙፍነቱወደር እንደሌለው በሚነገርለትበሰሜን ጀርመን ፣ በሃኖፈር ከተማ፣ በተዘጋጀውበዘንድሮው የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ትርዒት ፣ ዐቢይ የመነጋገሪያ ርእስ የሆነው።ከትናንት በስቲያ ተከፍቶ እስከ ከነገ በስቲያ ለሕዝብ ዕይታ ክፍት ሆኖ በሚቆየው የሃኖፈሩ ዓለም አቀፍ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ትርዒት ፤ የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ ምክትል፣ መተማመንና አስተማማኝ ሁኔታ በሚል ርእስ ንግግር ማሰማታቸው፤ በብዙዎቹ የኮምፒዩተር ትርዒት ማሳያ አዳራሾች ፣ ከመረጃ ሥነ ቴክኒክ ጋር በተያያዘ መልኩ፣ «አስተማማኝ አያያዝ » የሚሉ መፈክሮች መታየታቸው፤ የመረጃ ቴክኖሎጂ አስተማማኝ አያያዝ ቀያሽ የሚሰኙት ኦይግን ካስፔርስኪም በሃኖፈሩ ትርዒት መገኘታቸው፤ የዶቸ ቨለ ባልደረባ ሄንሪክ በኧመ፣ እንዳለው፣ በዩናይትድ ስቴትሱ ብሔራዊ የስለላ ድርጅት(NSA) የተወሰደው እርምጃ ያስከተለው ድንጋጤ አለመረሳቱን ነው። ትርዒት ማቅረቢያውን በሥፍራው ተገኝተው የጎበኙት ፤ የአውሮፓው ሕብረት የመረጃ ሥነ ቴክኒክ የዲጂታል ጉዳዮች ኀላፊ ኔደርላንዳዊቷ ኔሊ ክሮስ፣ የአውሮፓ የመረጃ ሥነ ቴክኒክ ኩባንያዎች ከአንቅልፍ ሊነቁ ይገባል ማለታቸው ተጠቅሷል። ኩባንያዎቹም ወዲያው የነቁ መስለው ታይተዋል። በጀርመን ቴሌኮም ፣ የመረጃ ቴክኖሎጂ ክፍል ኀላፊ ራይንሃርት ክሌመንስ--

Cebit 2014 Hannover Messeplakate
ምስል DW/J. Schmeller

«በጀርመን የተሠራ» (MAD

E IN GERMANY) ስለአስተማማኝ ጉዳይ ሲያነሣ፤ አንዳንድ መመዘኛዎች አሉት። የመጀመሪያው ለጀርመን የመረጃ ጥበቃን አስተማማኝ ማድረግ ነው ። ይህም ማለት፤ ተጠራቅመው የሚቀመጡ መረጃዎችን ማንም እንደፈለገ ፤ እንበል እዚህ ላይ የውጭ መረጃ አቅራቢ፣ ለፈለገው ጉዳይ ሊጠቀምባቸው አይችልም። ሁለተኛው ነጥብ፤ ከውጭ የሚሰነዘር ጥቃትን እንከላከላለን። ባልተፈቀደ መንገድ መረጃውን ለማግኘት የሚደረግ ጥረትንም ይከላከላል። እዚህ ላይ የሙያ ብቃት ነው የሚጠየቀው። የጀርመን ቴሌኮም፣ ከአነስተኛ ኩባንያዎች በላቀ ሁኔታ የተለየ ዕድገት ያሳየ መሆኑ እሙን ነው። ከሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የሚደረገው የልምድና ዕውቀት ልውውጥም ራሱን የቻለ አስተዋጽዖ ያደርጋል።»

መረጃዎች ከሚቀመጡባቸው CLOUDS ከሚሰኙ የኮምፒዩተር ግምጃ ቤቶች፣ የተለያዩ ኩባንያዎችም ሆኑ ግለሰቦች፤ ምሥጢራዊ ሰነዶችን በቀላሉ ማግኘትም ሆነ መውሰድ አይችሉም። ኤትሊንገን ከተባለችው ከባደን ቩርተንበርግ ፌደራል ክፍለ ሀገር ከተማ «ኢጎሴኩር» የተባለው 50 ሰዎች የሚገኙበት ኩባንያ ኀላፊ ሰርጌይ ሽሎትሃዎር---

«በእርግጥ ያለው አንድ ጠቀሜታ፤ የጀርመን ኩባንያ እንደመሆኑ መጠን፣ ለ NSA ም ሆነ ለሌላ የውጭ ክፍሎች ልዩ የመግቢያ በር እንደሌለ ደንበኞቻችን ማረጋገጥ ይችላሉ። ይህም ደግሞ በአሁኑ ጊዜ አስፈላጊ ነው። ለምን ቢሉ፣ በዩናይትድ ስቴትስ ኩባንያዎች ላይ አመኔታው እጅጉን ተሸርሽሯልና!በሌላም በኩል የጀርመን «ሶፍትዌር » በጀርመን ብቻ ሳይሆን በሌሎችም የዓለም ክፍሎች ምጥቀት በማሳየት ላይ ነው። በእስያና በላቲን አሜሪካ ብዙ ሥራ አለን። እነርሱም ከአሜሪካ አይደለም ሶፍትዌር የሚሹት! የአሜሪካው መረጃ ሰነድ መጠበቂያ እንደታሰበው ሆኖ አላገኙትም። እናም የጀርመን ሶፍትዌር፣ እፁብ ድንቅ ፣ እፁብ ድንቅ ነው ይላሉ»።

በሃኖፈር በመካሄድ ላይ ባለው የስማርትፎንስ፤ ኮምፒዩተርና የመሳሰሉ የኤሌክሮኒክስ ዕቃዎች ትርዒት ከዚህ ቀደም ለጀርመን ባለስልጣናት ጭምር የአጅ ስልኮች ያቀርብ የነበረው ኖኪያ ፤ አዲሱ ስልኩ በእጅጉ የተለወጠ የ«ብላክቤሪ » ዓይነት ሲሆን፤ «የሜርክል ፎን» የሚል ተቀጥላ ስምም ተሰጥቶታል። እናም 2,500 ይኸው ልዩ የእጅ ስልክ ባለፈው መጸው ተሸጧል። ለአስተማማኝነቱ ሲባልም ዋጋው በጣም ውድ መሆኑ ተመልክቷል። እያንዳንዱ ዋጋው 2000 ዩውሮ ነው ። ማናንኛውም መረጃ ከዚህ ሞባይል ወደ ሌላ ያለፈቃድ እንዳይዛወር «ሴኩስማርት» የተባለ አስተማማኝ ቁልፍ ያለው ነው ተብሏል።

Deutschland CeBit 2014 IT Sicherheit
ምስል DW/H. Böhme

በሓኖፈሩ ትርዒት፣ አውሮፓውያን በራሳቸው በመመካት የራሳቸውን ረቂቅ የሥነ ቴክኒክ ውጤቶች ለማቅረብ መነሣሣታቸው የታየበት ከመሆኑም ሌላ የአንዳንድ አስገራሚ ሰው መሰል ሮቦቶች ተግባር ታይቷል። አንድ በደቡብ ምዕራብ የጀርመን ከተማ በካርልስሩኸ የሚገኝ የቴክኖሎጂ ተቋም፤ የእጅ ሹራብ ሳያወልቁ ፣ አጫጭር መልእክቶችን በእጅ እንቅሥቃሴ ብቻ ማስተላለፍ የሚያስችል እጅ ላይ እንደ ሰዓት የሚታሠር ንዑስ መሣሪያ ሠርቶ አቅርቧል።

(ይቀጥላል)

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ