1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዓለም አቀፍ ችግር እየሆነ የመጣዉ የግብር ማጭበርበር

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 8 2007

ከጥቂት ወራት ወዲህ አንድ የተደበቀ ነገር ግልፅ እየሆነ መጥቷል። ይኸዉም በርካታ ትላልቅ ኩባንያዎች እና የንግድ ድርጅቶች ለመንግሥት በሕጉ መሠረት ገቢ ማድረግ የሚገባቸዉን ግብር ላለመክፈል በስዉር ያሸሻሉ ተብለዉ በብዙ ሃገራት ተከሰዋል።

https://p.dw.com/p/1E6Ll
Symbolbild Steuerflucht
ምስል picture alliance/blickwinkel

ባንኮችና ራሳቸዉ ብዙ ሚሊዮን ብር የሚያንቀሳቅሱት የኳስ ቡድኖችም እንዲሁ ተጠርጥረዉ ክስ ተመስርቶባቸዋል። አፍሪቃ ዉስጥ ሀብታቸዉን የሚያፈሱ ከብርቴዎችና ኩባንያዎችም ተመሳሳይ ሥራ ያካሂዳሉ ተብለዉ ተጠርጥረዋል። ይህንን ዉስብስብ ጉዳይ አስመልክቶ ባለፈዉ ሳምንት በርሊን ላይ አንድ ስብሰባ ተካሂዷል። የበርሊኑ ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለሚካኤል በስፍራዉ ተገኝቶ የግብር ፍትህ ያስፈልጋል የሚለዉን ዓለም አቀፍ ድርጅት የሚወክሉትን ኢትዮጵያዊ የልማት ኤኮኖሚ ባለሙያ ዶክተር ደረጀ አለማየሁን በማነጋገር ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ