1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዋሽንት ተጫዋቹ ኤርሚያስ ናደው

ሐሙስ፣ ሐምሌ 24 2006

በቀላሉ ሊሰሩ ከሚችሉ የሙዚቃ መሣሪያዎች አንዱ ዋሽንት ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በገጠሩ አካባቢ ሰዎች ገና ከልጅነታቸው ጀምሮ ነበር ከቀርቀሀ የተሰራች ዋሽንታቸውን ይዘው ሙዚቃ ሲጫወቱ የሚስተዋሉት።

https://p.dw.com/p/1CmW7
Washint Ermias Nadew
ምስል Ermias Nadew

ወጣት እና የአዲስ አበባ ከተማ ልጅ የሆነው ኤርሚያስ ናደዉ እንደቀልድ የተማረዉ ዋሽንት ጨዋታ ዛሬ መተዳደሪያዉ መሆኑን ይናገራል። ኤርሚያስ «ዋሽንት መጫዎቴ ለባህሌ ያለኝን ትኩረት አጠንክሮታል» ይላል።

የ25 ዓመቱ ኤርሚያስ እና ዋሽንት የተዋወቁት በአጋጣሚ ነበር። ከዛም ዋሽንት መጫወቱን ሊገፋበት ወሰነ። በወቅቱ የሚያውቀው የኪቦርድ መሣሪያ አስተማሪውን ነበርና ወደዛው አቀና። ትንሽም ስለ ዋሽንት ተማረ።

Washint Ermias Nadew
ምስል Ermias Nadew

ኤርሚያስ ከዋሽንት ጋር ቢተዋወቅ እና ለመጫወት ቢሞክርም፤ የከተሜ ልጅ መሆኑ ብዙ ገፍቶ እንዲቀጥል መጀመሪያ ላይ እልድ አልሰጥ ብሎት እንደነበር ነው የሚናገረው።

አንዳንዶች ዋሽንት ይዞ ስለሚጫወት ልጅ ሲያስቡ፤ በአይምሮዋቸው ተፀርፆ የተቀመጠ አንድ ነገር አለ።ይህም አጠር ያለ ቁምጣ ያደረገ ፣ ጥላ ላይ አንድ ዛፍ ስር ተጠልሎ ከቀርቀሀ የተሰራ ዋሽንት የሚነፋ ሰው ነው። ስለሆነም ኤርሚያስ ከመድረክ ሲወርድ ግራ የሚጋቡ ተመልካቾች አይጠፉም። ከጊዜ ጋር ግን ምስሉ ብቻ ሳይሆን የዋሽንቱም አይነት ተቀይሯል።

ኤርሚያስ ስራዬ ብሎ ባይዘውም እንደ ሦስተኛ የሙዚቃ መሣሪያ ባህላዊ ክራርም ይሞክራል። ከሌሎች መሣሪያዎች ሁሉ ዋሽንትን የመረጠበትን ምክንያት አጫውቶናል።

ኤርሚያስ በባህል የምግብ አዳራሾች ብቻውን የሚጫወተውን ዋሽንት ለጊዜው በCD መልክ ለማውጣት እቅድ በሀሳብ ደረጃ ቢቆይም በድምፅ እየተጫወተ በለበያ ሊያውል ያሰበው ነጠላ ዜማ አለው። ዝግጅቱን በድምፅ ዘገባ ያገኙታል።

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ