1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዉኃን ለጤና መጠጣት

ማክሰኞ፣ ግንቦት 4 2007

ዉኃ መጠጣት ለጤና እጅግ ተስማሚ መሆኑን የጤናም ሆኑ የስነምግብ ባለሙያዎች አዘዉትረዉ ይናገራሉ። ዉኃን የመጠጣት ልማድ ግን ብዙዎች የላቸዉም። በቀን ከሁለት ሊትር በላይ የሚጠጡ እንዳሉ ሁሉ አንዳንዶች እንደዉም አይጠማንም ይላሉ? እርስዎስ ከየትኛዉ ይሆኑ?

https://p.dw.com/p/1FOpF
Wasser im Glas
ምስል Colourbox

«ጤና ከገንዘብ ዉኃን ከቀለብ የሚቆጥረዉ የለም» ይላሉ አበዉ። ለዚህም ይመስላል ብዙዎች ለምግብ እና ለሌሎች መጠጦች የሚሰጡትን ስፍራ ያህል ለዉኃ ሲሰጡ የማይታየዉ። ዉኃ ስለመጠጣት ልምዳችሁ አጋሩን ስንል በፌስ በኩክ ገጻችን ላይ ላቀረብንላችሁ ጥያቄ የሰጣችሁት ምላሽም እንደተመለከታችሁት ይህንን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። በየዕለቱ አስበዉ በቂ ዉኃን የመጠጣት ልምድ ያላቸዉ ብዙዎች አይደሉም። ሲቀልዱ ይሁን ወይም ከምር ለማወቅ ቢከብደንም በሳምንት አንዴ ያሉ፤ ዉኃ በፈረቃ በሆነባት ከተማ ዉኃን እንደልብ መጠጣት የማይታለም እንደሆነ የጠቆሙ፤ ንፁሕ የመጠጥ ዉኃን ማግኘት ቅንጦት የሆነበት አካባቢ መኖሩን ያስረዱም አልጠፉም። የዉኃ እንደልብ አለመገኘት ግን ዉኃ ለሰዉነታችን ጤና ወሳኝ መሆኑን አያጎድለዉም። ግን የተከበሩ አድማጮቻችን ያነሷቸዉ የመሠረተ ልማትና ማኅበራዊ ጉዳዮች ከሚመለከተዉ አካል ትኩረትን የሚሹ መሆናቸዉ አያነጋግርም። ይህን ርዕሰ ጉዳይ ያነሳንበት ዓላማ ዉኃ በጤንነታችን ላይ ስለሚኖረዉ ሚና ለማሳሰብ በመሆኑ እሱዉ ላይ እናተኩር። ከድምፅ ዘገባዉ ያድምጡ

Symbolbild Limonade
ምስል imago/Chromorange

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ