1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ክርክር ያስነሳዉ የግብፅ መሪ የጀርመን ጉብኝት

ሐሙስ፣ ግንቦት 13 2007

የጀርመን መንግሥት የፊታችን ግንቦት 26 እና 27 የግብፅ ፕሬዝደንት ጀርመንን እንዲጎበኙ ያቀረበዉ ግብዣ የሀገሪቱን ፖለቲከኞች የጋራ ስምምነት አላገኘም።

https://p.dw.com/p/1FTs5
Deutschland Ägypten Steinemeier bei al-Sisi
ምስል picture-alliance/EPA/K. Elfiqi

[No title]

የጀርመን ታህታህ ምክር ቤት አንደኛ ፕሬዝደንትና አፈ ጉባኤ የሆኑት ኖርበርት ላመርት የፕሬዝደንት ሲሲን ጉብኝት እንደሚቃወሙ እሳቸዉን በእንግድነት መቀበልም ለሰብዓዊመብቶች ጥሰት ጆሮ አለመስጠት መሆኑን የሚዘረዝር ደብዳቤ በበርሊን ለግብፅ ኤምባሲ ማላካቸዉ ተሰምቷል። የግብጽ ፍርድ ቤት የቀድሞዉ የግብፅ ፕሬዝደንት ሞሀመድ ሙርሲና ሌሎች አንድ መቶ እስረኞች ከእስር ቤት ለማምለጥ ሲያሴሩ ተደርሶባቸዋል በሚል የሞት ቅጣት በይኗል። የጀርመኑ ፖለቲከኛ ይህንን አጥብቀዉ ተችተዋል። የሀገሪቱ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ግን አል ሲሲን ተቀብለዉ ለማነጋገር ዝግጁነታቸዉን ይፋ አድርገዋል። የአልሲሲ የጀርመን ጉብኝት ሃሳብ በጀርመን ፖለቲከኞች መካከል ያስነሳዉን አለመግባባት በሚመለከት በርሊን የሚገኘዉ ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለሚካኤልን ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ይልማ ኃይለሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ