1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኪየቭ፤ የተባባሰዉ የዩክሬን ቀዉስና የአዉሮጳ ኅብረት

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 7 2006

የአዉሮጳ ኅብረት ሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ለመጣል ተስማማ። በሉክዘምበርግ ትናንት የተሰባሰቡት የኅብረቱ የ28 ሃገራት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ንብረት የማንቀሳቀስና የቪዛ እገዳ ለማሳረፍ በሙሉ ድምፅ መስማማታቸዉ ተገልጿል።

https://p.dw.com/p/1BjCk
Ukraine Ostukraine Krise ukrainische Armee 15.4.2014
ምስል REUTERS

ሚኒስትሮቹ ሰሞኑን በምስራቅ ዩክሬን ግዛቶች የሚካሄደዉን ሕገወጥ የታጣቂዎች እንቅስቃሴ አዉግዘዋል። የአየርላንድ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሞን ጊልሞር ሩሲያ እንቅስቃሴዉን በይፋ እንደማትቀበለዉ እንድትገልፅ ጠይቀዋል። ማዕቀቡ ስንት የሩሲያ ባለስልጣናትን እንደሚመለከት ከመዘርዘር የተቆጠቡት የአዉሮጳ ኅብረት የዉጭ ጉዳይ ፖሊሲ የበላይ ካትሪን አሽተን ሞስኮ የዩክሬንን የድንበር ሉዓላዊነት በማክበር ወታደሮቿን እንድታስወጣ በኅብረቱ ስም ጥሪ አስተላልፈዋል።

«ይህ ዩክሬንን የማተመስሙከራመቆምይኖርበታል። የዩክሬንንህብረት፣ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት አጥብቀን እንደግፋለን። ሩሲያም እንዲሁ ይህንኑ በማድረግ ከዩክሬን ድንበር አካባቢ ወታደሮቿን እንድትመልስ ጥሪ እናቀርባለን።»

EU Verteidigungsminister Treffen in Luxembourg 15.04.2014 Ursula von der Leyen
ምስል picture alliance/AP Photo

የብሪታንያ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዊልያም ሄግ በበኩላቸዉ ሩሲያ ከዩክሬን ጋ የገባችበትን ዉዝግብ በዲፕሎማሲ ለመፍታት ፈቃደኛ መሆኗን ባለማሳየቷ 28ቱ የአዉሮጳ ኅብረት አባል ሃገራት ተጨማሪ ማዕቀብ እንዲጣል መስማማታቸዉ ትክክል ነዉ ይላሉ፤

«ሁኔታዉን ለማርገብ ዲፕሎማሲ ለመጠቀም መዘጋጀቷን ለማሳየት ወሳኝ አጋጣሚ ነበር፤ እንዲያም ሆኖ ያን የሚጠቁምርምጃከሩስያወገንእስካሁንአንዳችምልክትአልታየም።እናምዛሬተጨማሪማዕቀብ ለመጣልመስማማታችንትክክልነዉ።»

በተቃራኒዉ ሩሲያ ዩክሬን ዉስጥ በተባባሰዉ ወደራሺያ ያደላ እንቅስቃሴና የፀጥታ መደፍረስ እንደሌለችበት ደጋግማ ትገልጻለች። በዛሬዉ ዕለትም ካትሪን አሽተን ከዩናይትድ ስቴትስ፣ ከሩሲያ እና ዩክሬን የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋ ስዊትዘርላንድ ላይ ተገናኝተዉ እንደሚነጋገሩ ይጠበቃል። የአራቱ ባለስልጣናት የዛሬ ዉይይት ሩሲያን አሳምኖ ከዩክሬን እንድትወጣ ካላደረጋት ማዕቀቡ ባስቸኳይ ተግባራዊ እንደሚሆን የፈረንሳይ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሎሮ ፋቢዮ አመልክተዋል።

በሌላ በኩል የዩክሬን ታጣቂ ሠራዊት በሀገሪቱ ምሥራቃዊ ክፍል በምትገኘዉ ክራማቶርስክ ከተማ በተገንጣዩ ቡድን ላይ «ልዩ ዘመቻ» መጀመሩን የሮይተር ዘገባ አመለከተ። የኢንተር ፋክስን የዜና ወኪል የጠቀሰዉ ይህ ዘገባ ከተጠቀሰችዉ ከተማ የጦር አዉሮፕላን ማረፊያ አካባቢ የእሩምታ ተኩስ እንደሚሰማና ተዋጊ ጀቶችም ሲያንዣብቡ መታየታቸዉን የአካባቢዉ ጋዜጠኞችን ዋቢ አድርጓል። በሌላ በኩል የዩክሬን አዉሮፕላን በስፍራዉ እንዳታርፍ የመገንጠል ንቅናቄ የሚያካሂዱት ወገኖች ተኩስ እንዳገዳትም ተዘግቧል። የሩሲያ ወገንተኛ ታጣቂዎች የዩክሬን ወታደሮች እና ታንኮች በሚታዩበት በምሥራቅ ዩክሬን በተቆጣጠሯቿዉ ሕንፃዎች አካባቢ ይዞታቸዉን በማጠናከር አዳዲስ ማገጃዎችን ማስቀመጣቸዉ ተገልጿል። የዩክሬን ጊዜያዊ ፕሬዝደንት አሌክሳንደር ቱርቺኖቭ ተገንጣዮቹን የሚጠራርግ «ፀረ ሽብርተኛ ዘመቻ» ያሉትመጀመሩን አስታዉቀዋል።

Ostukraine Krise ukrainische Armee nahe Slawjansk 14.04.2014
ምስል picture-alliance/ITAR-TASS

«ዛሬ ጠዋት በዶኔስክ አካባቢ አንድ ፀረ ሽብር ዘመቻ ተጀምሯል። በድጋሚ አፅንኦት ለመስጠት የምፈልገዉ ይህ ዘመቻ የሚካሄደዉ የዩክሬን ዜጎችን ለመከላከል ነዉ። ከዚህ በተጨማሪም ሽብርና የወንጀል ተግባር እንዲያከትም ለማደረግ እና ዩክሬንን ለመቆራረስ የሚፈልጉትን ለማስቆም ነዉ።»

ከዚህም ሌላ ሩሲያ ዩክሬንን ለማቀጣጠል እየሠራች ነዉ ሲሉ ከሰዋል። የሩሲያ ፕሬዝደንት ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፒስኮቭ በበኩላቸዉ የሞስኮ ወታደሮች ቀዉስ ዉስጥ በተዘፈቁት የዩክሬን ግዛቶች የሉም ሲሉ አስተባብለዋል።

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ