1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እየሩሳሌም ባዲሱ ጥቃት ማግሥት

ሐሙስ፣ ኅዳር 11 2007

የእስራኤል መንግሥት የገዳዮችን፤የወላጆቻቸዉንና የዘመዶቻቸዉን መኖሪያ ቤቶች እያስፈረሰ ነዉ። የአንዲት ከተማ ከንቲባ ደግሞ አረብ እስራኤላዉያን በግንባታ ሥራ-እንዳይሰማሩ አግደዋል።

https://p.dw.com/p/1DqcM
ምስል picture-alliance/ dpa

ሁለት ፍልስጤማዉያን እየሩሳሌም የሚገኝ አንድ ምኩራብ ገብተዉ አራት ራባይ (የይሁዲ ሐይማኖት መሪዎችን) እና አንድ የእስራኤል ፖሊስን ከገደሉ ወዲሕ ወትሮም በቋፍ የሚገኘዉ የቅድስቲቱ ከተማ ሠላም ይበልጥ ታዉኳል።የእስራኤል መንግሥት የገዳዮችን፤የወላጆቻቸዉንና የዘመዶቻቸዉን መኖሪያ ቤቶች እያስፈረሰ ነዉ።የእስራኤል መንግሥት በቅርቡ ከተፈፀመዉ ጥቃት በተጨማሪ ከዚሕ ቀደም ሌላ ሥፍራም አስራኤላዊ ገድለዋል የተባሉ ፍልስጤምችን፤ የወላጆጃቸዉንና የዘመዶቻቸዉን ቤቶችም እያስፈረሰ ነዉ።የአንዲት ከተማ ከንቲባ ደግሞ አረብ እስራኤላዉያን በግንባታ ሥራ-እንዳይሰማሩ አግደዋል።የእየሩሳሌሙ ተባባሪ ዘጋቢያችን ዜናነሕ መኮንን እንደሚለዉ እየሩሳሌም መበቃቀሉ ይባባሳል በሚል ሥጋት እንደተወጠረች ነዉ።

ዜናነሕ መኮንን

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ