1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢጣሊያ በምታድናቸው ተገን ጠያቂዎች ላይ የተነሳው ቁጣ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 14 2006

የኢጣሊያ ባህር ኃይል ባለፉት 48 ሰዓታት ብቻ 1000 ስደተኞችን ከመስመጥ ማትረፉን አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/1BmGV
Italien Flüchtlingsdrama Lampedusa
ምስል picture alliance/dpa

በሜዲትራኒያን ባህር በኩል ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ወደ ኢጣሊያ የሚገቡት ስደተኞች የማዳኑ ተልኮ እንደ ኢጣሊያ መገናኛ ብዙኃን ከሆነ በወር 9 ሚሊዮን ዩሮ ድረስ ያወጣል። የጎርጎሪዮሳዊዉ 2014 ከገባ ባለፉት አራት ወራት ብቻ 22 ሺ ስደተኞች ኢጣሊያ መግባታቸው ይነገራል። ይህ ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ10 እጥፍ ጨምሯል። ታድያ አንዳንድ ሁኔታው ያበሳጫቸው የኢጣሊያ ፓርቲ መሪዎች፤ የማዳኑ ተልኮ ጉዳይ ማቆም ያስፈልጋል የሚል ሀሳብ እስከመሰንዘር ደርሰዋል። ኢጣሊያ በምታድናቸው ተገን ጠያቂዎች ላይ የተነሳውን ቁጣ አስመልክቶ ሸዋዬ ለገሰ ሮም የሚገኘው ዘጋቢያችን ተክለእዝጊ ገብረ እየሱስን በስልክ አነጋግራዋለች።

ተክለእዝጊ ገብረ እየሱስ

ልደት አበበ

ሸዋዬ ለገሰ