1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አወዛጋቢው የአባይ ግድብ ፕሮጀክትና የኢትዮጵያና የግብፅ ንግግር

እሑድ፣ ሐምሌ 20 2006

ግብጽ አሁንም እንደ ከዚህ ቀደሙ ግድቡ ወደ ሃገርዋ በሚገባው የውሃ መጠን ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳያደርስ ያቀረበችው ጥያቄ እንዴት እንደሚፈታ እያጠያየቀ ነው

https://p.dw.com/p/1Cj7Y
Nil Dammbau in Äthiopien Archiv 28.05.2013
ምስል William Lloyd-George/AFP/Getty Images

የኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን የጎረቤት ሃገራትን የኤሌክትሪክ ፍላጎት ያሟላል በተባለው በግዙፉ የአባይ ግድብ ፕሮጀክት ላይ ኢትዮጵያና ግብፅ ከዚህ ቀደም ጀምረው ያቋረጡትን ንግግር ለመቀጠል መስማማታቸው በግንባታው ሰበብ የተነሳውን ውዝግብ በሰላም የመፍታት ተስፋ ተጥሎበታል ። ሆኖም ግብጽ አሁንም እንደ ከዚህ ቀደሙ ግድቡ ወደ ሃገርዋ በሚገባው የውሃ መጠን ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት እንዳያደርስ ያቀረበችው ጥያቄ እንዴት እንደሚፈታ እያጠያየቀ ነው ።አወዛጋቢው የአባይ ግድብ ፕሮጀክትና የኢትዮጵያና የግብፅ ንግግር የዛሬው እንወያይ ትኩረት ነው በዚህ ጉዳይ ላይ የሚወያዩ 2 እንግዶችን ጋብዘናል። አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እንዲሁም አቶ ዩሱፍ ያሲን የቀድሞ ዲፕሎማት እና ተንታኝ በውይይቱ ይሳተፋሉ ።

ሂሩት መለሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ