1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አነጋጋሪው የሲፕራስ የሩስያ ጉብኝት

ረቡዕ፣ መጋቢት 30 2007

ግሪክ ከዓለም ዓቀፍ አበዳሪዎች ጋር በብድር አከፋፈልና አሰጣጥ ላይ አንድ መቋጫ ላይ ላይ ከመድረስዋ በፊት ሲፕራስ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ሆድና ጀርባ ወደ ሆነችው ወደ ሩስያ መሄዳቸው ጥያቄዎች አስነስቷል

https://p.dw.com/p/1F4H7
Russland Griechenland Tsipras bei Putin
ምስል picture-alliance/dpa/Mikhail

ሩሲያና ግሪክ፤ በኃይል ምንጭ አቅርቦት ረገድ ተቀራርበው ለመሥራት ተስማሙ።የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሲስ ሲፕራስ ዛሬ የጀመሩት የሁለት ቀናት የሩስያ ጉብኝት እዚህ አውሮፓ ማነጋገሩ ቀጥሏል። የጉብኝታቸው ዓላማ የሁለቱን ሃገራት የኤኮኖሚ ትብብር ፣ የመዋዕለ ንዋይ ፍሰትና የንግድ ግንኙነቶች ማጠናከር መሆኑ ተገልጿል ። ሆኖም ግሪክ ከዓለም ዓቀፍ አበዳሪዎች ጋር በብድር አከፋፈልና አሰጣጥ ላይ አንድ መቋጫ ላይ ላይ ከመድረስዋ በፊት ሲፕራስ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ሆድና ጀርባ ወደ ሆነችው ወደ ሩስያ መሄዳቸው ጥያቄዎች አስነስቷል ።የግሪክ ባለሥልጣናት በሲፕራስ የሞስኮ ጉብኝት የግሪክ ብድርና እዳ አከፋፈል ጉዳይ ትኩረት የሚሰጠው አይሆንም ሲሉ ተናግረዋል ።ከዚያ ይልቅ የውይይቶቹ ትኩረት የኃይል አቅርቦት ፣ውረታ ፣ንግድ ፣ቱሪዝምና እርሻ እንደሚሆን ነው ያስረዱት ።ሆኖም ሲፕራስ ከግሪክ ወደ ሩስያ በሚላኩ የእርሻ ምርቶች ላይ ሩስያ የጣለችውን ገደብ እንድታላላ መጠየቃቸው እንደማይቀር ተነግሯል ።ፕሬዚዳንት ፑቲንና የግሪኩ ጠ/ሚንስትር አሌክሲስ ሲፕራስ እንዳረጋገጡት የውይይታቸው ትኩረት ዕዳ የተቆለለባት ግሪክ የገንዘብ ድጋፍ ስለምታገኝበት ሁኔታ አልነበረም። ሲፕራስ የግሪክ ችግር የአውሮፓ ችግር በመሆኑ ሊፈለግለት የሚገባም አውሮፓዊ መፍትኄ ማለታቸው ተመልክቷል። በዩክሬይን ውዝግብ ሳቢያ አንዱ በሌላው ላይ የሰደውና አጸፋዊውም የኤኮኖሚ እገዳ መቆም አለበት ብለዋል። ፑቲን ፤ ሩሲያ ግሪክን ከሌሎች አውሮፓውያን ለመነጠል ትጥራለች የሚለውን ወሬ አጣጥለዋል። ሩሲያ የተቋረጠው የግሪክና የሩሲያ የንግድ ልውውጥ እንዲጠናከር እንዲሁም ገንዘብ ግሪክ ውስጥ ሥራ ላይ እንዲውል ለማድረግ ፍላጎቷ መሆኑን ገልጻለች። «ተርኪሽ ስትሪም » በተሰኘው የጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧ በሚዘረጋበት ፕሮጀክትም ግሪክ እንድትሳተፍ የሩሲያ ፍላጎት መሆኑም ተወስቷል። በአውሮፓው የአገዳ ርምጃ ሳቢያ የግሪክ የግብርና ውጤት ከባድ ሳንክ እንዳጋጠመው በተጨማሪ ተጠቅሷል።የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ በሁለቱ መሪዎች ንግግር ና ጉብኝቱ በአውሮፓ ህብረትና በአባል ሃገራቱ ዘንድ እንዴት እንደሚታይ የሚቃኝ ዘገባ አዘጋጅቷል።

Russland Griechenland Tsipras bei Putin
ምስል picture-alliance/dpa/Zemlianichenko

ገበያው ንጉሴ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሀመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ