1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አስቸጋሪው የደቡብ ሱዳን ውዝግብና ሽምግልናው

እሑድ፣ ኅዳር 14 2007

ነጭ ዐባይ አቋርጦ የሚያልፍባት የተፈጥሮ ውበትና የደለበ የተለያየ የማዕድናት ሀብት ያላት ፤ ደቡብ ሱዳን ፣ ነጻነት አውጃ 2 ዓመት ከመንፈቅ ከተጓዘች በኋላ ፣ ፕሬዚዳንቷ ሳልቫ ኪር ፣ አምና ታኅሳስ 6 ቀን 2006 ዓ ም፤ መፈንቅለ መንግሥት

https://p.dw.com/p/1DrOP
ምስል picture-alliance/Minasse Wondimu/Anadolu Agency

ሊካሄድብኝ ነበር ሲሉ በቀድሞው ምክትላቸው ሪክ ማቻርና ደጋፊዎቻቸው ላይ ከተነሱ ወዲህ ፣ ደቡብ ሱዳናውያን ፣ ባልታሰበ ሁኔታ፣ በእርስ በርስ ጦርነት እንደገና ፍዳ ሲያዩ እንሆ አንድ ዓመት ሊሞላ ነው።

ይህን ደም አፋሳሽ ውዝግብ ለመግታትና ሰላም መልሶ እንዲሠፍን ለማድረግ የአፍሪቃ ሕብረት በተለይም የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት አባል ሃገራት በመሸምገል አያሌ ወራት ቢያሳልፉም ፣ እስካሁን የተፈለገው ውጤት ሊገኝ አልቻለም። ለምን? ውጊያው ካልተገታ ፣ ሰላምም ካልሠፈነ የደቡብ ሱዳን ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል? በአጎራባች ሃገራት የሚያስከትለው ተጽእኖስ እንዴት ይታያል? አብነቱ ምንድን ነው? «አስቸጋሪው የደቡብ ሱዳን ውዝግብና ሽምግልናው»፣ በሚል ርእስ ፣ዶቸ ቨለ ለዚህ ሳምንት ባዘጋጀው ውይይት 3 እንግዶች ተሳትፈዋል ፣ እነርሱም ፣ በደቡብ ሱዳን የኢጋድ የተቆጣጣሪና አጣሪ ቡድን ዋና ኀላፊ አቶ ተፈራ ሻውል፣ የአፍሪቃ የፀጥታ ጥናት ተቋም ተመራማሪ ፤ አቶ ሃሌ ሉያ ሉሌ፣ እንዲሁም የአዲስ አበባው የዶቸ ቨለ ዘጋቢ ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ናቸው።

ተክሌ የኋላ

ልደት አበበ