1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አሳሳቢው የደቡብ ሱዳን ውጊያ

ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 11 2006

በደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች በቦር፣ ጆንግሌይ የሚገኘውን የተመድ ሰፈር አጥቅተው ቢያንስ 50 ሰዎች ገደሉ። በዚሁ ቢያንስ 5000 ሰዎች ከለላ ባገኙበት ሰፈር በተጣለው ጥቃት ከቆሰሉት መካከልም ሁለት የተመድ ሰላም አስከባሪዎች ይገኙባቸዋል።

https://p.dw.com/p/1BkqJ
Südsudan UN-Camp in Bor
ምስል AFP/Getty Images
Südsudan Rebellen 10.02.2014
ምስል Reuters

በደቡብ ሱዳን የፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር ተቀናቃኝ የሆኑት የቀድሞው ምክትል ፕሬዚደንት ሪክ ማቸር ታማኝ ኃይላት በነዳጅ ዘይት የታደለውን የዩኒቲ ግዛት ዋና ከተማ ቤንትዊን ሰሞኑን ከመንግሥት ወታደሮች አስለቅቀው መልሰው መያዛቸውን እና በዚያ በነዳጅ ዘይት ኢንዱስትሪው ውስጥ የሚሰሩ የውጭ ኩባንያዎች ስራቸውን እንዲያቆሙ ማስጠንቀቃቸውንም የቡድኑ ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀነራል ሉል ሩዋይ አስታውቀዋል። ሀምሌ 2003 ዓም ነፃነቷን ካገኘች ወዲህ መረጋጋት የተሳናት የደቡብ ሱዳን መንግሥት ቃል አቀባይ ፊሊፕ አግዌር ግን ቤንትዊ መያዟን ሀሰት ሲል አስተባብሎዋል።

ውዝግቡ ከተጀመረ ወዲህ ከአንድ ሚልዮን የሚበልጥ ሰው ከመኖሪያ ቀየው ተፈናቅሎዋል። እንደሚ ታወቀው ፣ ሀገሪቱ ጥገኛ የሆነችበት የነዳጅ ዘይቱ ኢንዱስትሪ ባለፈው ታህሳስ ወር በፕሬዚደንቱ እና በቀድሞው ምክትላቸው መካከል በተፈጠረው የሥልጣን ሽኩቻ ውጊያ ከተጀመረ ወዲህ ስራው ተስተጋጉሎ፣ ምርቱ በ20% ቀንሶዋል።

አሁን ቤንትዊ መያዟ የቀጠለውን ውዝግብ እንደሚያባብሰው በቦን የሚገኘው « ኢንተርናሽናል ሴንተር ፎር ኮንቨርሽን» የተባለው የፖለቲካ ጥናት ተቋም ባልደረባ ወይዘሮ ኤልከ ግራቨርት አስረድተዋል።

Sudanesische Flüchtlinge in Äthopien Kule Flüchtlingslager
ምስል DW/Coletta Wanjoyi

« ዓማፅያኑ ዋነኛ የደቡብ ሱዳን የገቢ ምንጭ የሆኑትን የነዳጅ ዘይት ንጣፎች ከያዙ ይህ የሥልጣኑን ሽኩቻ ይበልጡን ያጠናክረዋል። የአፐር ናይልን ግዛት ዋና ከተማ ማላካልን ዓማፅያኑ ከያዙ በኋላ የመንግሥቱ ጦር ወዲያው መልሶ ተቆጣጥሮ ነበር፣ ጥቂት ቆይቶ ግን ዓማፅያኑ ከተማዋን መልሰው ይዘዋል። በቤንትዊም የታየው ተመሳሳይ ነው። ዋናው ጥያቄ ግን ሁለቱ ተፋላሚ ወገኖች እንዴት ነው ከዚሁ በሥልጣን ሽኩቻ ሰበብ ከገቡበት ውጊያ የሚላቀቁት የሚለው ነው። »

በዚያም ሆነ በዚህ የነዳጅ ዘይት ንጣፎች በዓማፅያኑ ቁጥጥር እየገቡ ከሄዱ ይህ መንግሥት አሁን የሚከተለውን አካሄድ እንዲቀይር ላይ ሊያስገድደው እንደደሚችል ወይዘሮ ግራቨርት ይገምታሉ።

« ዓማፅያኑ ንጣፎቹን መቆጣጠራቸውን ከቀጠሉ ይህ መንግሥቱ ለውዝግቡ አንድ መፍትሔ እንዲያፈላልግ ጫና ያሳርፍበታል። መፍትሔው ወታደራዊ መፍትሔ ሊሆን ይችላል። እኔ እስካሁን እንደማየው፣ ለሁለቱም፣ ለመንግሥትም እና ለ ለዓማፅያኑ የርስበርሱ ጦርነት ዋናው አማራጭ ነው ።

Öl Raffinerie in Juba, Sudan
ምስል Hannah Mcneish/AFP/Getty Images

በድርድር ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲያፈላልጉ ካልተገደዱ በስተቀር የርስበርስ የሚጀምርበት ስጋታ አለ። ቀድሞ በሱዳን ለ22 ዓመታት በተካሄደው የርስበርስ ጦርነት ወቅት ደቡባዊው ሱዳን ከነዳጅ ዘይት የሚያገኘው ገቢ አልነበረም። እና ወደዚያ ሁኔታ ካለነዳጅ ዘይቱ ገቢ፣ ከውጭ ሊያገኙት በሚችሉ የጦር መሳሪያ ርዳታ እና በርዳታ የሚያገኙትን ለውጊያው ተግባር በማዋል ወደለፈው ዓይነቱ የርስበርሱ ጦርነት ሊያመሩ የሚችሉበት ሁኔታ እንዳፈጠር ያሰጋል። እና ኢጋድ ተፈላሚዎቹ ወገኖች ባለፈው ጥር ወር የደረሱትን የተኩስ አቁም ደምብ ባለማክበራቸው አሁን አንድ የተኩስ አቁሙን የሚቆጣጠር ኃይል ለማሠማራት ነው እየሞከረ ያለው። ኢጋድ ሁለቱን ወገኖች እንደገና ወደ ድርድሩ ጠረጴዛ የማምጣት ትልቅ ሚና ሊጫወት ይችላል። ግን፣ ከሚመለከታቸው ተፋላሚ ወገኖች በኩል ያን ያህል ፈቃደኝነታ አይታይም። እንደሚመስለኝ ፣ ወታደራዊውን መፍትሔ አስቀድመዋል። እና «ኤስፒኤልኤም» የነዳጅ ዘይቱን ንጣፎች በጦሩ ርምጃ ማስመለስ የሚፈልግ ይመስለኛል።

አርያም ተክሌ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ