1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተቃውሞና ግጭት በባህር ዳር

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 13 2007

በባህር ዳር ከተማ ዓርብ ታኅሣሥ 10 ቀን 2007 ዓም ድንገት በተቀሰቀሰ ግጭት ከሦስት እስከ አምስት ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ተሰማ። በርካቶችም መቁሰላቸው ተጠቅሷል። ሆኖም የደረሰዉን የጉዳት መጠን በትክክል የሚያረጋግጥልን የመንግስት አካል አላገኘንም።

https://p.dw.com/p/1E8pz
ምስል picture alliance/Peter Groenendijk/Robert Harding

የግጭቱ መንስዔ በባህር ዳር ከተማ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በበዓላት ቀናት የታቦታ ማደሪያ እንደሆነ የሚነገርለት መስቀል አደባባይ ለሌላ ሥራ ሊውል ነው በሚል መሆኑም ተዘግቧል።ጉዳዩን በቅርበት እንደተከታተሉ የገለፁልን እማኞች የግጭቱ መንስዔ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በተለያዩ የበዓላት ቀናት ለታቦት ማደሪያነት የምትጠቀምበት የመስቀል አደባባይ በመንገድ ማስፋፊያ የተነሳ ሊታረስ ነው በሚል መሆኑን ይናገራሉ።

Blue Nile, Map, english
ምስል CC/Lourdes Cardenal

በዓርብ ዕለቱ ግጭት በተቃውሞ ሰልፉ ያልተሳተፉ ሆኖም ከተማው ውስጥ የነበሩ ሌላ የባህር ዳር ነዋሪ በበኩላቸው ከግጭቱ በፊት እና በኋላ ስለተከሰተው የሚያውቁትን አብራርተዋል። በግጭቱ የሞቱ እና የቆሰሉ ሰዎች መኖራቸውን ተናግረዋል።

በግጭቱ የሞቱ ሰዎችን ቁጥር በውል ለማወቅ የባህር ዳር ከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አላዩ ጋር ደወልን። አገኘናቸው። ስብሰባ ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው መልሰን እንድንደውል ነገሩን። ሆኖም በገቡልን ቃል መሰረት በእጅ ስልካቸው ላይ በተደጋጋሚ ብንደውልም ስልኩ ሊነሳ አልቻለም። ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትንም ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ ከታች የሚገኘውን የድምፅ ማጫወቻ ይጫኑ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ