1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቫቲካን እና የአዛውንቱ ኢትዮጵያዊ አርበኛ ጥያቄ

ረቡዕ፣ መስከረም 7 2007

ሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተጀመረበት 75 ኛ ዓመት ከጥቂት ጊዚያት በፊት መታሰቡ የሚታወስ ነው። ይሁንና፣ ኢትዮጵያውያን የታሪክ ምሁራን ፣ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተጀመረው ፋሺስት ኢጣልያ የዓለም መንግሥታት

https://p.dw.com/p/1DETL
Feier 118. Schlacht von Adua
ምስል Getachew T. Haile-Giorgis

ማኅበር አባል የነበረችውን ብቸኛዋን አፍሪቃዊት ሀገር ኢትዮጵያን ከ79 ዓመት በፊት በወረረበት ጊዜ መሆኑን ነው የሚናገሩት። በዚሁ የኢጣልያ ወረራ ላይ ቫቲካን በከፊል ድርሻ እንዳላትም ምሁራኑ ይገልጻሉ። ፋሺስት ኢጣልያ በኢትዮጵያ ላይ ባካሄደው ወራራ ብዙ ሕዝቧ ማለቁ እና ከፍተኛ ጥፋት መድረሱ የሚታወቅ ነው። ኢጣልያ በዚያን ጊዜ ወረራ ለደረሰው ጥፋት ኢትዮጵያን እስከዛሬ ይቅርታ አልጠየቀችም፣ ካሳም አልከፈለችም። እና ይህን በተመለከተ አዛውንቱ ኢትዮጵያዊ አርበኛ ጀነራል ለማ ገብረማርያም ሰሞኑን ለቫቲካን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ግልጽ ደብዳቤ ልከዋል። ይህንኑ መነሻ በማድረግ ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ የአርበኞች ማኅበር ፕሬዚደንትን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ