1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቤጂንግ፤ በተበከለ አየር ማራቶን ተካሄደ

እሑድ፣ ጥቅምት 9 2007

የተበከለ አየር ባጠላባት የቻይና መዲና ቤጂንግ ውስጥ በተካሄደ የማራቶን ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያን አሸናፊ ሆኑ። በውድድሩ ወደ 25000 የሚጠጉ ሯጮች ተሳታፊ መሆናቸውም ተዘግቧል።

https://p.dw.com/p/1DYSw
Smog in Peking
ምስል Reuters/J. Lee

የዓለም የአትሌቲክስ ውድድርን የቻይና መዲና ቤጂንግ ልታስተናግድ አንድ ዓመት ገደማ ሲቀረው ዛሬ የተበከለ አየር በሞላበት ሰማይ የማራቶን ውድድር ተካሄደ። እንደዚያም ሆኖ በሴቶችም ሆነ በወንዶች የማራቶን ሩጫ ውድድር ኢትዮጵያውያን አሸናፊ ሆነዋል። በሴቶች ማራቶን ፋጡማ ሳዶ ዴርጎ፣ በወንዶች ደግሞ ግርማይ ብርሃኑ ገብሩ ናቸው ውድድሩን በአሸናፊነት ያጠናቀቁት። 25 000 የሚጠጉ የውድድሩ ተካፋዮች፣ የአየር ብክለቱን ለመከላከል ፊታቸው ላይ ጭንበል አድርገው መሮጣቸው ተገልጿል። ውድድሩ ሲጀመር የአየር ብክለቱ 400 ሚክሮ ግራም በኪውቢክ ሜትር የነበረ ሲሆን፤ እንደ የዓለም የጤና ድርጅት ከ25 ሚክሮ ግራም ጀምሮ የተበከለ አየር ለጤና ጎጂ ነው። የውድድሩ አዘጋጆች ግን ዝግጅቱን ሳይሰርዙ ሩጫው ተካሂዷል። የቻይና መዲና ከመኪናዎች በሚለቀቁ የተቃጠሉ ጋዞች ከመበከሏ ባሻገር ከተማዋ ከፍተኛ የድንጋይ ከሠል ኃይል ጥገኛ ናት።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ልደት አበበ