ቢራና ቦርጭ፣
ረቡዕ፣ የካቲት 26 2006የሚመረተው ፣ የሚጠጣውም የዚያኑ ያክል ነው። ለምሳሌ ያህል፤ ጣቢያችንና እኛም የምንገኝባትን ሀገር ጀርመንን እንውሰድ ፤--- ግንባር ቀደምት ከሆኑት ቢራ ጠማቂ ሃገራት አንዷ ናት ። በተለይ በራይን ወንዝ ዳርቻ በሚገኙ ታላላቅ ከተሞች፤ በይበልጥ በካርኒቫል የፈንጠዝያ ሳምንት ፣ በኮሎኝ ፤ ዱሰልዶርፍ፤ ማይንትዝና ፣ ሌሎች ሥፍር ቁጥር በሌላቸው ንዑሳን ከተሞች፤ በሙዩኒክ ፣ ደግሞ ፣ በያመቱ ፣ በመስከረም ወር አንድ ወር ያህል ቢራ በገፍ የሚጠጣበት የደቡብ ጀርመኑ Oktoberfest የተሰኘው ወቅትም ሌላው፣ ቢራ በጀርመን ያለውን ተወዳጅነት የሚያሳይ ክብረ በዓል ነው። በዓል ሲኖር መጠኑ ከመጨመሩ በስተቀር ፤ ጀርመን ውስጥ ቢራ በማንኛውም ጊዜ ፤ በቤትና በመሸታ ቤቶች የሚዘወተር መጠጥ መሆኑ እሙን ነው። በሀገሪቱ በመላ ፣ ከ 5,000 በላይ የተለያየ የቢራ ዓይነት መኖሩም የታወቀ ሲሆን፣ እያንዳንዱ ጀርመን ፣ በያመቱ ፣ በነፍስ ወከፍ ከ 115,5 ሊትር የማያንስ ቢራ ይጠጣል። ከአውሮፓ ጀርመን 3ኛ ናት፤ በነፍስ ወከፍ የቢራ ፍጆታን ካሰላን ፣ በአውሮፓ ቀዳሚውን ቦታ የሚይዙት ቼኮች ናቸው። በነፍስ ወከፍ በያመቱ 157 ሊትር ቢራ ነው በዚያች ሀገር የሚጠጣው። አየርላንድ በ 131,1 ሊትር 2ኛ፤ ናት ። ከአፍሪቃ ፣ ደቡብ አፍሪቃ በአንደኛነት፤ ከዓለም ደግሞ 29 በመሆን ፣ ህዝቧ በነፍስ ወከፍ በዓመት 63 ሊትር ቢራ ይጠጣል።
ከደቡብ አፍሪቃ ቀጥሎ በአፍሪቃው ክፍለ ዓለም ውስጥ ማለት ነው፤ አንጎላ፣ ናሚቢያ ፣ ኬንያ ፣ ታንዛንያና ዩጋንዳ ብዙ ቢራ በመጠጣት መጀመሪያ ረድፍ ላይ ይገኛሉ። ዩጋንዳ ከዓለም 47ኛ ከአፍሪቃ 6ኛ ስትሆን ፣ በዚያች ሀገር በዓመት በነፍስ ወከፍ 6 ሊትር ቢራ ነው የሚጠጣው። በኢትዮጵያ ከዚያ በታች ነው ፤ በዓመት በነፍስ ወከፍ 4 ሊትር ቢራ!
ቢራ በብዛት የሚጠጡ ሰዎች ፣ በተለይ ወንዶች የሆድ ዕቃ ውፍረት ይታይባቸዋል!ቦርጭ !
ጀርመናውያን ፣ «ቢር ባውኽ» እንግሊዞች «ቢር ቤሊ» የሚሉት መሆኑ ነው። ቢራ ለምን ቦርጫም ያደርጋል ? ለምን በሴቶች ላይ ይህ ያን ያህል አይታይም? ባለሙያ አነጋግረናል። እርሳቸውም፤ የምግብ ይዘት ምርምር ነክ ሳይንስ ባለሙያ ወይም የሥነ ምግብ ባለሙያ አቶ አብነት ተክሌ ናቸው።
ተክሌ የኋላ
ኂሩት መለሰ