1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጀርመን ፖሊሶች ላይ ዘረኝነት?

ሐሙስ፣ ኅዳር 18 2007

ፈርግሰን-ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ ያልታጠቀ ጥቁር ወጣትን የገደለዉ ነጭ ፖሊስ እንዳይከሰስ የከተማይቱ ፍርድ ሸንጎ መወሰኑ የቀሰቀሰዉ ሕዝባዊ ቁጣና ተቃዉሞ እንደቀጠለ ነዉ። ጀርመንም ቢሆን ፖሊሶች በቆዳ ቀለም ከፍተኛ የዘር መድሎ ያደርጋሉ በሚል በተደጋጋሚ ይወቀሳሉ።

https://p.dw.com/p/1DvUd
Videostill Polizeikontrolle in Bonn
ምስል DW

ለዚህ ተጠቃሹ ደግሞ በቅርቡ የተጋለጠዉና በህቡዕ ይንቀሳቀስ የነበረዉ ቅኝ ፅንፈኛዉ ብሔራዊ ሶሻሊስት ቡድን «NSU» አባላት በተደጋጋሚ የፈፀሙትን የግድያ ወንጀል ፖሊስ ማድበስበሱ ነዉ። በርግጥ በጀርመን ፖሊሶች ዘንድ የዘር መድሎ ይደረግ ይሆን?
በጀርመን ፖሊሶች የስራ ልምድ መሰረት አንድ የድብደባ ወንጀል ከተፈፀመ ብዙዉን ግዜ ጥርስ ዉስጥ የሚገቡት ከሩስያ የመጡ ነዋሪዎች ናቸዉ። ቤት ሰብሮ በመግባት በሌብነት በዘረፋ የሚታወቁት ደግሞ ከሌሎች የምስራቅ አዉሮጳ ሐገራት ወደ ጀርመን የገቡ ናቸዉ። የመኖርያ ፈቃድ ሳይኖራቸዉ ያለህግ ይኖራሉ ተብሎ የሚታመነዉ ደግሞ ጥቁሮች ወይም አፍሪቃዉያን ናቸዉ። መንጃ ፈቃድን ጨምሮ በተሽከርካሪ ላይ ስለደረሰ ማንኛዉም አይነት ወንጀል የሚጠረጠሩትና መኪናቸዉ ላይ ፍተሻ የሚደረገዉ ከደቡባዊ አዉሮጳ በመጡ ላይ ብቻ ነዉ። እንዲህ አይነቱ የፖሊስ እምነትና አሰራር ከየት መጣ በሚል የጀርመን የፖሊስ ለራሱ ባደረገዉ አንድ ጥናት ያገኘዉ መልስ ፖሊሶች የወንጀል ሥራቸዉን በፍጥነት በማካሄድ ተሰራ ለተባለ ወንጀል መልስ ማግኘት ስላለባቸዉና ባለባቸዉ ከፍተኛ የሥራ ጫና መሆኑ ተመልክቶአል። በጀርመንም ቢሆን በዩናይትድ ስቴትስ ሚዙሪ ግዛት-ፈርግሰን ከተማ የተካሄደዉ አይነት የዘር መድሎ ርምጃ እንዳለ የሚያሳየዉ አንድ በህቡዕ ይንቀሳቀስ የነበረዉ ጽንፈኛ የቀኝ አክራሪ ቡድን የተደጋጋሚ የግድያ ወንጀል እጅግ ዘግይቶ እዉነታዉ መገኘቱ ተጠቃሽ ነዉ። በተደጋጋሚ የግድያ ወንጀል የፈፀሙት ቀኝ አክራሪዎቹ የብሔራዊ ሶሻሊስት ቡድን አባላት የገደሏቸዉ አብዛኞቹ የቱርክ ዝርያ ያላቸዉ ነጋዴ ወንዶች ናቸዉ። የጀርመን የሥለላ መስሪያ ቤት ይህን ወንጀል በተመለከተ፤ ከወንጀሉ በስተጀርባ አንድ የቱርክ ተወላጆች የሚያንቀሳቅሱት የማፍያ ቡድን ፀብ መሆኑንና በወንጀሉ የሟቾች ቤተሰብ አባላት አሉበት ብሎ ደምድሞም ነበር። በፊደራል ጀርመን የፖሊስ ቢሮ የሰራተኛ ማኅበር ተጠሪ ራይነር ቬንድት እንደሚሉት ከዚህ ተደጋጋሚ የግድያ ወንጀል በስተጀርባ በውጭ ዜጎች ጥላቻ የተሞሉት የአፍቃሬ ናዚዎች ቡድን መሆኑን « ፖሊስ ያልተጠበቀዉና የማይሆን » ብሎ ያመነበት ነገር ነበር» ሲሉ ተናግረዋል። ለዚህ ምክንያታቸዉ ደግሞ፤ «ዘረኝነት አለ ተብሎ ቢወራም ዘረኝነት የለም። ፖሊስ ጥረት እያደረገ ያለዉ ለመኮንኖች የተለያዩ ባህሎች አብሮነትን በስልጠና ያሳያል። ይህ ብቻ አይደለም ፤ በአዲስ የሚመጡ ባህላዊ እንቅስቃሴዎችንም ለመኮንኖች በየግዜዉ ያስተዋዉቃል። ምክንያቱም ሀገራችን የተለያዩ ባህል ያላቸዉን የዓለም ሃገራት ማኅበረሰቦች ሰብስባ የምትገኝ በመሆንዋ ነዉ። ስለዚህም ፖሊሶች በሥራ ላይ በሆኑበት ጊዜ እነዚህ መጤ ባህሎችን ማክበር እንዲችሉ ያስችላቸዋል»
ከሰሜን እስከ ደቡባዊ ጀርመን የሚገኙ ታዋቂ ፖለቲከኞች ሁሉ በሀገሪቱ ከአስር ዓመታት በላይ የዘርኝነት ችግር የለም። የሌለን ችግር ለመፍታት ደግሞ አንነሳም ብለዉ ድምዳሜ ላይ ለደረሱ ፖለቲከኞች ሀገሪትዋ ዉስጥ የዘረኝነት ችግር ይታያል ብሎ እላይ ለተቀመጡት የሀገር አስተዳደር ሚኒስትር መናገሩ እጅግ ከባድ መሆኑን የሀገሪቱ የፖሊስ መስርያ ቤት የሰራT,Na ማኅበር ተጠሪ ራይነር ቬንድት ተናግረዋል። ለምሳሌ በኖርድ ራይን ቬስፋልያ ግዛት ምን ያህል ጀርመናዊ፤ ምን ያህል የዉጭ ሃገር ዜጋ ወንጀል ሰራ ተብሎ የሚደረገዉ ጥናት ይፋ ሆኖ ለማኅበረሰቡ እንዲቀርብ አይፈለግም። ምክንያቱም እንዲህ አይነቱ የጥናት መረጃ ግዛቲቱን ለሚያስተዳድሩት SPD (ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ) እና ለአረንጓዴዎቹ ፓርቲዎች አይስማማቸዉም፤ በዚህም ምክንያት ተድበስብሶ መታለፉን ገልፀዋል።
በጎርጎርጎረሳዉያኑ 2010 የአዉሮጳዉ ሕብረት በአዉሮፕላን ጣብያ ፤ በድንበር ጥበቃ እና በባቡር ጣብያ በተደረጉ የመታወቅያ ቁጥጥሮች ላይ ከፀጥታ ጥበቃ መስርያ ቤት ያገኘዉን መረጃ አሰባስቦ ባደረገዉ ጥናት በአብዛኛዉ የዉጭ ዜጎች ላይ ቁጥጥር መደረጉን አመላክቶአል። የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል በበኩሉ በጥናቱ ዉጤት መሰረት የታየዉ ቁጥጥሩ የሰብዓዊ መብትን የተጋፋ ነዉ ሲል ይወቅሳል። በፊደራል ጀርመን የፖሊስ መስርያ ቤት የሰራተኛ ማኅበር ተጠሪ ራይነር ቬንድት የአምንስቲን ክስ ሚዛናዊ ያልሆነ ሲሉ አጣጥለዋል። እንደ ራይነር ቬንድ የጀርመን መንግሥት ህገ-ወጥ ሁኔታ ወደ ሀገሪቱ የገቡ ዜጎች ላይ ቁጥጥር እንዲደረግ በህግ ፈቅዷል
« አንዳንድ መቀበል የሚገባን ነገሮች አሉ። ለምሳሌ ከዉጭ የመጡ ሰዎች ብቻ ሊያደርጉት የሚችሉት ወንጀል አለ-ለምሳሌ ህገ-ወጥ የሆነ ፍልሰት። ይህን ሊያደርግ የሚችለዉ ማን እንደሆነ ይታወቃል። ለምሳሌ የመኖርያ ፈቃድ ቁጥጥርን በተመለከt። እንበል አንድ የ 80 ዓመት ጀርመናዊት አዛዉንት ወይም አንድ የ20 ዓመት አፍሪቃዊ ወጣት ቢኖሩ እዚህ ላይ መኖርያ ፈቃድ እንዲያሳይ የሚጠየቀዉ ማን እንደሆነ ለማንም ግልፅ ነዉ። ይህን በተመለከተ የጀርመን ፊደራል ፖሊስ ህጋዊ በሆነ መንገድ እንዲሰሩ ከህግ አዉጭዎች በቀረበ አሰራር ታዘዋል። ተግባራቸዉን በሚከናዉኑበት ጊዜም ህጉን በመከተል የራሳቸዉን ሃሳብ ይጠቀማሉ። ይህ ታድያ ከዘረኝነት ጋር በምንም አይገናኝም»
በሌላ በኩል ይህን አይነት ወንጀል ከዚህ ሀገር የመጣ ሰዉ ነዉ የሰራዉ፤ ይህን አይነት ወንጀሎች የሚሰሩት ከዚህ ሀገር በመጡ ሰዎች ነዉ የሚሰሩት ብሎ የማሰቡ ነገር በፖሊሶች አሰራር ላይ ይታያል። ይህ አይነቱ አስተሳሰብ ሊጤንበትና ወጣት ፖሊሶች እንዲህ አይነቱ ሃሳብ ሥራቸዉ ላይ ስህተት እንዳያስከትል ስልጠና ሊሰጣቸዉ እንደሚያስፈልግ ተመልክቶአል። ስለዚህም በታህታይ ዛክሶንያ ግዛት በሚገኘዉ የፖሊስ ማሰልጠኛ አካዳሚ አንድ የምርምር እቅድ ተይዞአል። በጥናቱ ፖሊሶች በመረጃ ያልተደገፈ ዉንጀላንና ተሞክሮዎቻቸዉን ያሰባስባሉ። ቢሆንም ይህ አይነቱ ጥናት ሊያመጣ የሚችለዉ መዘዝ ስጋት ላይ በመጣሉ ፤ ከጎርጎረሳዊዉ 1996 በኋላ ጥናቱ ሳይደረግ መቅረቱም ተዘግቦአል። ከጎርጎረሳዉያኑ 2013 ጀምሮ በታህታይ ዛክሶንያ በሚገኘዉ የፖሊስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ዉስጥ ዳግም የተጀመረዉን ጥናት የሚመሩት ፕሮፊሰር አስትሪድ ያኮብ ስለጥናቱ ዉጤት በሰጡት ቃለ ምልልስ አብዛኞቹ ፖሊሶች በወንጀል ነክ ነገሮች በሃሳባቸዉ ስለዉ ያስቀመጥዋቸዉ ነገሮች፤ በጀርመን ማኅበረሰብም ቢሆን እንዲሁ የሚታሰቡና የሚታመንባቸዉ ጉዳዮች ናቸዉ ሲሉ ተናግረዋል። ለዚህ ደግሞ ዋናዉ ምክንያት አብዛኞቹ ፖሊሶች የመነጩት መካከለኛ ገቢ ካላቸዉ የጀርመን ማኅበረሰብ ዉስጥ በመሆኑ ነዉ። መካከለኛ ገቢ የሚያገኘዉ የጀርመን ማኅበረሰብ የተስተካከለ ኑሮን እየኖረ በዉጭ ሃገር ዜጋ ኑሮዉ እንዳይስተጓጉልበት ስጋት ስለላለዉ በመጤዎች ላይ ያለዉ በመረጃ ያልተደገፈ ወንጅላ እጅግ የተስፋፋ ነዉ።

Sondereinsätzkräfte der Polizei
ምስል picture-alliance/dpa/Karl-Josef Hildenbrand
Symbolbild Zug Bundespolizei Kontrolle
ምስል picture-alliance/dpa
Rainer Wendt, Bundesvorsitzender der Deutschen Polizeigewerkschaft
በፊደራል ጀርመን የፖሊስ ቢሮ የሰራተኛ ማኅበር ተጠሪ ራይነር ቬንድትምስል picture-alliance/dpa


ዎልፍጋንግ ዲክ / አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ