1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በደቡብ አፍሪቃ በውጭ ዜጎች ላይ የተሰነዘረው ጥቃት

ዓርብ፣ ሚያዝያ 9 2007

የደቡብ አፍሪቃ መንግሥት በውጭ አገር ሰዎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት እና ተቃውሞ ለማስቆም የሚቻለውን ሁሉ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል። ይሁንና በተለይ ከሌሎች የአፍሪቃ ሀገራት በሄዱ የውጭ ዜጎች ላይ በደርባን ከተማ የሚደርሰው ጥቃት ተባብሶ የኢኮኖሚ ማዕከል የሆነችው ጆሀንስበርግ ከተማም ተስፋፍቷል።

https://p.dw.com/p/1F9da
Ausländerfeindliche Ausschreitungen in Durban, Südafrika
ምስል Reuters/R. Ward

በደቡብ አፍሪቃ በውጭ አገር ዜጎች አንፃር የተጀመረው አዲስ ጥቃት ሁለት ሳምንት አለፈው። እስካሁን አንድ ኢትዮጵያዊ እና ሌሎች 4 ሰዎች ሞተዋል። የጥቃቱ ዓይነት እና ተቃውሞ ክፉኛ ተጠናክሯል።በተለይ ከሌሎች የአፍሪቃ ሀገራት በሄዱ አፍሪቃውያን ላይ የሚደርሱት ጥቃቶች እየተጠናከሩ የሄዱት የደቡብ አፍሪቃ የዙሉ ብሔር ንጉስ፤ ጉድዊል ዝዌሊቲኒ የውጭ ዜጎች ሻንጣቸውን ይዘው ሀገሪቷን ይልቀቁ ብለዋል የሚለው መልዕክት ከተሰራጨ በኋላ መሆኑን ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

« የዙሉ ብሔር አባላት የሆኑ ደቡብ አፍሪቃውያን ንጉሱ የውጭ ሀገር ዜጎች ወደሀገራችው መመለስ አለባችው ብለዋል ሲሉ ከነገሩን በኋላ፤ ይደበድቡን ጀመር። ኃላም ሱቆቻችንን ዘርፈው፤ ንብረታችንንም ነጥቀውናል። እኛ ምንም አቅም ስላልነበርን ፖሊስ ጠራን። ፖሊስ ሁኔታውን ሊቆጣጠር አልቻለም። ከዛ ወደ ፖሊስ ጣቢያ በመውሰድ ከለላ ሰጥተውናል።»ይላል፤ አንዱ በደርባን ከተማ የሚገኝ አፍሪቃዊ ። የዙሉ ብሔር ንጉስ ፤ ሀገር ለቀው ይውጡ ያሉት ማንኛውንም ስደተኛ ሳይሆን፤ ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ወንጀል የሚፈፅሙትን ማለታቸው እንደሆነ ኃላ ላይ ግልፅ አድርገዋል። ይሁንና ይህ በውጭ ዜጎች ላይ ያነጣጠረውን አሳሳቢ ጥቃት አላበረደውም።

Ausländerfeindliche Ausschreitungen in Durban, Südafrika
በውጭ ዜጎች ላይ የተዘነዘረውን ጥቃት በመቃወም የተደረገ ሰላማዊ ሰልፍምስል Getty Images/Afp

በደቡብ አፍሪቃ በውጭ ሀገር ዜጎች ላይ ጥላቻ ወይም «ዜኖ ፎቢያ» የታየው እኢአ በ2008 ዓም ነው። በወቅቱ 62 ሰዎች ሲሞቱ ከነዚህም ውስጥ 4oዎቹ የውጭ ሀገር ዜጎች ነበሩ። ከዚያን ጎዜ በኋላም በተለይ ከከተማ ወጣ ብሎ በሚገኙ አካባቢዎች በርካታ ሰዎች ተገድለዋል።

Friedensmarsch in Durban Südafrika
የደቡብ አፍሪቃ ፖሊስምስል Reuters/R. Ward

53 ሚሊዮን ገደማ ህዝብ ባላት ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ቁጥራቸው እስከ 5 ሚሊዮን የሚገመት ስደተኞች ይኖራሉ። አብዛኞቹም ለተሻለ ኑሮ ሲሉ በህጋዊ እና በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሀገሪቱ የተሰደዱ ወጣት አፍሪቃውናን ናቸው። በርካታ ወጣት ኢትዮጵያውያን ለተሻለ ኑሮ ሲሉ የተሰደዱባት ደቡብአፍሪቃእና በአሁኑ ሰዓት ከሌሎች የአፍሪቃ ሀገራት በሄዱ የውጭ ዜጎች ላይ ስለሚፈፀመው በደል ከድምፅ ዘገባው ያድምጡ።

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ