1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በስደተኞች ላይ ያተኮረ ዓውደ ጥናት በብራስልስ

ዓርብ፣ መስከረም 16 2007

በአዉሮጳ ሀገራት ለስደተኞች የሚከራከሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች ሰሞኑን ለሁለት ቀናት የዘለቀ ዓውደ ጥናት ብራስልስ ላይ አካሂደዋል።

https://p.dw.com/p/1DLf4
Flüchtlinge Lampedusa
ምስል picture alliance / ROPI

ሴሚናሩን ያዘጋጀው በስደተኞች ጉዳይ የሚንቀሳቀሱ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እናት ድርጅት የሆነዉ የአዉሮጳ የስደተኞች ምክር ቤት ሲሆን፤ ዓላማዉ የድርጅቶቹን አቅም፤ በማሳደግ እና አሰራራቸዉንም በማቀናጀት የተሻለ ሥራ ሊሰሩበት የሚችሉበት ሆኔታን ለመፍጠር ነዉ። የዓውደ ጥናቱ ተካፋዮች በአዉሮጳዉ ምክር ቤትም ተገኝተዉ ወደ አዉሮጳ ለመግባት ሲሞክሩ ህይወታቸዉ ስለሚያልፈዉ ተገን ጠያቂዎች እንዲሁም ስደተኞቹ አዉሮጳ ከደረሱ በኋላ ስለሚደርስባቸዉ መንገላታት በማስረዳት ሕብረቱ በስደተኞች ላይ የሚከተለዉ ፖሊሲ ከመንግሥታቱ ድርጅት እና ከራሱ ከአዉሮጳ ሕብረት የስደተኞች መብት ድንጋጌዎች ጋር የተጣጣመ እንዲሆን አሳስበዋል። የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዘገባ ልኮልናል።


ገበያዉ ንጉሴ
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ