1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በርካታ ስደተኞች ሜዲትሬንየን ባህር ሰጠሙ

ማክሰኞ፣ መስከረም 6 2007

ባለፉት ሶስት ቀናት ከአፍሪቃ እና ከመካከለኛዉ ምሥራቅ ወደ አዉሮጳ ለመግባት ያቀዱ ቁጥራቸዉ ወደ 800 የሚጠጉ ተገን ጠያቂዎች ሜደተራንያን ባህር ሰጥመዉ ለህልፈት መዳረጋቸዉ ኢጣልያ ሮማ የሚገኘዉ ሀገራት አቀፍ የስደተኞች ድርጅት እንዲሁም የተመ የስደተኞች ጉዳይ ቢሮ ይፋ ያደረጉት መግለጫ ያመለክታል።

https://p.dw.com/p/1DDUm
Italien Flüchtlingsdrama Lampedusa Flüchtlingsboot
ምስል picture-alliance/ROPI

ከግብፅ ከፍልስጤም እና ከሶርያ የመጡ 500 ስደተኞችን የጫነ መርከብ ፤ ከግብፅ ዳሜትያ ወደብ ተነስቶ ሜዲተራንያን ባህር ላይ እየተንሳፈፈ ሳለ፤ ህገ-ወጥ አዘዋዋሪዎቹ ግለሰቦች፤ ስደተኞቹ ጀልባ እንዲቀይሩ ሃሳብ አቅርበዉ፤ ተገንጠያቂዎቹ ስላልተስማሙ በመካከላቸዉ አለመግባባት ተፈጥሮ አዘዋዋሪዎቹ ጀልባዉን ሆን ብለዉ ማስመጣቸዉ ታዉቋል። ሁለት ፍልስጤማዉያን ወጣቶች ለበርካታ ሰዓታት ባህር ላይ ከቆዩ በኋላ ፓጉስ በተባለ መርከብ ድነዉ ደቡባዊ ጣልያን ምስክርነታቸዉን ሰጥተዋል። የዓለም አቀፍ የስደተኞች ጉዳይ ድርጅት ባወጣዉ ዘገባ በዚህ ዓመት ብቻ ወደ አዉሮጳ በጀልባ ለመግባት የሞከሩ ወደ 3000 ያህል ተገን ጠያቂዎች ባህር ዉስጥ በመስጠም ህይወታቸዉን አጥተዋል። በሌላ ዜና፤ ሊቢያ ጠረፍ አቅራቢያ እንደገና በሚያሰቅቅ ሁኔታ 250 ያህል ስደተኞች ሳይሰጥሙ እንዳልቀሩ ተነገረ። ከሊቢያ ባህር ኃይል በኩል እንደተገለጠው ከሆነ 250 ያህል አፍሪቃውያን ስደተኞችን ያሣፈረ ጀልባ ሰጥሟል። እስካሁን የ26 ሰዎችን ሕይወት ማትረፍ ተችሏል። የባህር ኃይሉ ቃልአቀባይ እንዳለው፣ የብዙ ሰዎች አስከሬን ባህር ላይ ሲንሳፈፍ ታይቷል። የባህር ላይ ስደተኞች የሰሞኑን አደጋ በተመለከተ፤ ሮም ኢጣልያ የሚገኘዉ ወኪላችን ተክለዝጊ ገብረየሱስ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።


ተክለዝጊ ገብረየሱስ
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ