1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በርሊን ማራቶን- አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ተሰበረ

እሑድ፣ መስከረም 18 2007

ዛሬ በጀርመን በርሊን ከተማ በተካሄደው የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያቱ ትርፊ ፀጋዬ እና ፈይሴ ታደሰ ተከታትለው በመግባት አንደኛ እና ሁለተኛ ወጡ። በእዚሁ የበርሊኑ የማራቶን ሩጫ ፉክክር ኬንያዊው ዴኒስ ኪሜቶ የዓለም ክብረ ወሰን ሰብሯል።

https://p.dw.com/p/1DMMZ
41. Berlin Marathon 28. Sept. 2014 Kimetto Weltrekord
ምስል TOBIAS SCHWARZ/AFP/Getty Images

30 ዓመቱ ኬንያዊ 41 ጊዜ በጀርመን መዲና በተካሄደው የማራቶን ውድድር (2: 02: 57) በመሮጥ ከዓለም 2 ሰዓት 03 ደቂቃ በታች ከሮጡ ሰዎች የመጀመሪያውም ሆኗል። ዴኒስ ኪሜቶ በሀገሩ ዜጋ ዊልሰን ኪፕሳንግ ተጠብቆ የነበረውን የዓለም ክብረ ወሰን 26 ሰከንድ አሻሽሏል። በውድድሩ ኬንያዊው ኤማኑኤል ሙታይ 2ኛ፣ ኢትዮጵያዊው አበራ ኩማ (2: 05: 56) 3 ሆነዋል። በውድድሩ ውጤት ያስመዘግባል በሚል በከፍተኛ ሁናቴ ሲጠበቅ የነበረው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ፀጋዬ ከበደ ውድድሩን አቋርጦ ወጥቷል። በበርሊኑ የሴቶች የማራቶን ውድድር ደግሞ ኢትዮጵያዊቷ ትርፊ ፀጋዬ (2: 20: 18) ሰከንድ በመሮጥ አሸናፊ ሆናለች የሀገሯ ልጅ የሆነችው ፈይሴ ታደሰ 2 ስትወጣ የዩናይትድ ስቴትሷ ሻለን ፍላንገን 3ኛነት አጠናቃለች። በውድድሩ ኢትዮጵያውያቱ ታደለች በቀለ እና አበበች አፈወርቅ 4 እና 5 በመሆን ውድድሩን አጠናቀዋል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ልደት አበበ