1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስልጣን የለቀቁት የቡርኪና ፋሶ መሪ

ዓርብ፣ ጥቅምት 21 2007

ቡርኪና ፋሶ ከፈረንሳይ ቅኝ ነጻ ከወጣችበት እ.ኤ.አ. 1984 ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የምታውቀው ሁለት መሪዎች ብቻ ነው። አፍሪካዊው ቼ ጉቬራ ይባሉ የነበሩት ቶማስ ሳንካራን እና ብሌዝ ኮምፓዎሬን ። ብሌዝ ኮምፓዎሬ ወደ ስልጣን የመጡት ቶማስ ሳንካራ በወታደሮች መገደላቸውን ተከትሎ እ.ኤ.አ. በ1987 ዓ.ም. ነበር።

https://p.dw.com/p/1DfJa
Burkina Faso Ex-Präsident Compaore Archiv 2011
ምስል picture alliance/AP Photo/R. Blackwell

ዛሬም ድረስ ግልጽ ባይሆንም በቶማስ ሳንካራ ግድያ እጃቸው እንዳለበት ይጠረጠራል። ወደ ስልጣን ሲመጡ ታጣቂዎችን ትጥቅ ማስፈታት እና የቀድሞ ጓደኛቸውና መሪያቸው ቶማስ ሳንካራ የሚከተሉትን ሶሻሊዝም አሽቀንጥሮ መጣል በቀዳሚነት ያከናወኗቸው ተግባራት ናቸው።

ኮምፓዎሬ እ... 1991 እና 1998 የተካሄዱ ሃገራዊ ምርጫዎችን አሸንፈዋል። እ... 2000 የወጣው አዲስ የቡርኪና ፋሶ ህገ-መንግስት የፕሬዝደንቱን የስልጣን ዘመን ለአስር አመት ብቻ ቢወስነውም ተጨማሪ ሁለት ምርጫዎችን ከማሸነፍ አላገዳቸውም። በሁሉም ምርጫዎች ከ80 በመቶ በላይ ድምጽ በማግኘት ነበር ያሸነፉት።

የሊቢያው የቀድሞ መሪ ሞዓመር ጋዳፊ እና የላይቤሪያው ቻርልስ ቴይለር ወዳጅ ነበሩ። ብሌዝ ኮምፓዎሬ እጃቸውን አስረዝመው በሌሎች ሃገሮች የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ይገባሉ እየተባሉ ይተቹም ነበር። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እ... 2000 .. በአንጎላ እና ሴራሊዮን ያሉ ተቃዋሚዎችን በጦር መሳሪያና አልማዝ ይረዳሉ ብሎ ከሷቸዋል።በተቃራኒው የፈረንሳይና አሜሪካም ወዳጅ ናቸው።

Burkina Faso Jubel nach dem Rücktritt des Präsidenten Compaore 31.10.2014
ምስል AFP/Getty Images/I. Sanogo

ኮምፓዎሬ ተቃውሞ ሲገጥማቸው የመጀመሪያ አይደለም። ከሶስት አመታት በፊት እንኳ የደሞዝ ማሻሻያ እና የተሻለ የኑሮ ሁኔታ እንፈልጋለን ያሉ ወታደሮች ተቃዋሚዎችን ተቀላቅለው ነበር። ይህ ግን የሰውየውን የስልጣን ፍቅር የሚገታው አልነበረም።

ኮምፓዎሬ ከ27 አመታት ፕሬዝዳንትነት በኋላ በቃኝ ለማለት አልደፈሩም።እናም ከጥቂት ወራት በኋላ በሚካሄደው ምርጫ ለመወዳደር እንዲያስችላቸው ፓርላማው ህገ-መንግስቱን ለማሻሻል እጁን አነሳ። የተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን በይሁንታ የሚቀበሉት አልነበረም። እናም 'አብዮት 2.0 ተቀሰቀሰ። ትዊተር የተሰኘው ማህበራዊ ድረ-ገጽ በቀዳሚነት የመወያያ መድረክ ሆነ። የቡርኪና ፋሶ ተቃዋሚ ፖለቲካ መሪዎች ዜጎች ተቃውሟቸውን እንዲያሰሙ፤ ወደ አደባባይ እንዲወጡ ጥሪ አስተላለፉ።መንገዶች በተቃዋሚዎች ተጥለቀለቁ፤በአደባባዮች መካከል የቆሙ የመታሰቢያ ሃውልቶች ፈረሱ፤ብሄራዊ የሬዲዮና ቴሌቭዥን ጣቢያውም ከጥቃት አላመለጠም።

ኮምፓዎሬ ተስፋ አልቆረጡም። እስከሚቀጥለው ምርጫ ድረስ የሽግግር መንግስቱን ለመምራት ጥያቄ አቀረቡ። ይህም ግን ተቀባይነት አላገኘም። ለተቃውሞ የዋና ከተማዋ ኡጋዱጉ ጎዳናዎች የወጡ ዜጎች ከኮምፓዎሬ ይልቅ በጡረታ የተገለሉት እና እ... 2004 .. ፕሬዝዳንቱን ለመገልበጥ አሲረዋል ተብለው የተከሰሱት የጦር አዛዥ ጄኔራል ክዋሜ ሎጉን እንፈልጋለን የሚል ድምጽ አሰሙ።

አሁን ኮምፓዎሬ ሙሉ በሙሉ የተሸነፉ ይመስላል። የቡርኪናፋሶ ጦር አዛዥ ፓርላማው መበተኑን፤የሽግግር መንግስት መቋቋሙንና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁን ይፋ አድርገዋል።

ኮምፓዎሬ ቡርኪናፋሶን ሲመሩ ስልጣን ሁሉ በእጃቸው ነበር። ጥቅላይ ሚኒስቴር ይሾማሉ። መንግስታዊ መዋቅሩና አገራዊ ጦሩ በእርሳቸው ጥብቅ ቅጥጥር ስር ነው።ራሳቸውን የሃገሪቱ መረጋጋት እና ኢኮኖሚያዊ እድገት ጠበቃ አድርገው ይቆጥራሉ። ይሰብካሉ።

አሁን ግን የልጅነት ጓደኛቸውን ገድሎ ለስልጣን ያበቃቸው የሃገሪቱ ጦር ለ27 አመታት የነገሱበትን መንበረ ስልጣን ነጥቋቸዋል።

እሸቴ በቀለ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ