1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስለ «በራሪ ፍጡራን» የሚነገረውና ሳይንሳዊው ሐቅ፣

ረቡዕ፣ ሐምሌ 9 2006

በፍጥረተ ዓለም ፣ በተለይ በዝች እኛ ከምንኖርባት ምድር (ፕላኔት) ውጭ በሌሎች ዓለማት እጅግ የrr,ቀቀ የራሳቸው ሥልጣኔ ያላቸው ፍጡራን ይኖሩ ይሆን? የሚታሰቡት ፍጡራን ቀለማቸው፣ አረንጓዴ፤ ይሁን ፤ ግዙፍ ይሁኑ ንዑስ፤ የሰው ቅርጽ ይኑራቸው የሌላ

https://p.dw.com/p/1CeDA
ምስል picture-alliance / dpa/dpaweb

፤ጋዝ ይሁኑ ዕብን፤ በገሐድ የሚያውቅ ማን አለ?ስንትና ስንት ቢሊዮን ፤ ትሪሊዮን ኪሎሜትር ርቀት ፣ ብሎም በቢሊዮን የብርሃን ዓመት የሚቆጠር ርቀት ካለው አካባቢ የሚመጡ ሊሆኑ ይችላሉ የሚባሉ ፍጡራን፣ እንዴት በአንድ ፣ ከሄሊኮፕተር በማይበልጥ ጎድጓዳ ሳህን መሰል በራሪ ነገር ህልውናቸው ተጠብቆ መንቀሳቀስ ይችላሉ? ምን ይተነፍሳሉ? ስንቃቸው ምንድን ነው? ምን ይመገባሉ? እንዴት ይራባሉ? የሚበሩበት መሣሪያስ የፀሐይን ግለትና የሚያኮማትር የሕዋን ብርድ የሚቋቋም እንዲሁም በቂ ቦታ ያለው ነው ወይ?

UFO
ምስል AP

እነዚህንና የመሳሰሉ ጥያቄዎች፤ ከሳይቤሪያ እስከ ሰሃራና ኮንጎ፤ ከአማዞን ጥቅጥቅ ደን ፣ፓታጎኒያ ኔፖልና ቲቤት ወይም እስከ ዑሉሩ አስገራሚ ወጥ የቀይ ድንጋይ ክምር የሚገኝበት የአውስትሬሊያ አውራጃም ሆነ በየትኛውም ቦታ የሚኖሩ ሰዎች ይህንና የመሳሰሉ ጥያቄዎች ቢያነሱ አያስደንቅም! በየአህጉሩ ብዙ ይባላልና! እኛም በዛሬው ሳይንስና ሕብረተሰብ ቅንብራችን ፣ በየጊዜው እንደሚታዩ ስለሚነገርላቸው በ«ጎድጓዳ ሣህን መሰል መሣሪያ » ይበራሉ ስለሚባሉ፣ አስገራሚዎቹ ፣ ሰው መሰል በራሪ ፍጡራን ምነንት ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚኖሩ ካንድ አድማጭ የቀረበ ጥያቄና አንድ የሳይንስ ምሁር የሚሰጡትን ምላሽ ይዘን ቀርበናል።

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ