1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎችና የአዉሮጳ ሕብረት እቅድ

ቅዳሜ፣ ግንቦት 8 2007

ከሊቢያ የባህር ወደብ አቅጣጫ የመጡ የጀልባ ስደተኞች ወደ አዉሮጳ ለመግባት ሜዲተራንያን ባህር ላይ ሰምጠዉ ካለቁ ወዲህ የአዉሮጳ ሃገራት መንግሥታት ለስደተኞች ይዞታ የተለያዩ ርምጃዎችን እየወሰዱ ነዉ። ተጨማሪ እቅድም አላቸዉ።

https://p.dw.com/p/1FQU8
Symbolbild Flüchtlingskatastrophe Mittelmeer
ምስል picture-alliance/dpa/E. Ferrari

የአዉሮጳዉ ሕብረት በቅርቡ በተስማማበት መሠረት ስደተኞችን ወደ አዉሮጳ በሚያዘዋዉሩ ሕገ- ወጥ አዘዋዋሪዎች ላይ ኃይልን የጨመረ ርምጃ ይወስዳል። ይሁንና ርምጃዉን በመዉሰድ ሕብረቱ የተመድ የፀጥታዉን ምክር ቤት ይሁንታ እየተጠባበቁ ነዉ። የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና የስደተኞች ጉዳይ ተከራካሪዎች ግን የአዉሮጳ ሕብረትን ዕቅድ በተለይም የአሸጋጋሪዎችን ጀልባዎች በጦር ኃይል ለማጥብቃት የሚደረገዉን ዝግጅት አጥብቀዉ ይተቻሉ። የዶቼ ቬለ ያነጋገራቸዉ «Grünhelme» የተሰኘዉ የጀርመን የርዳታ ድርጅት መስራችና ዋና ተጠሪ ሩፐርት ኖይዴክ እንደሚሉት ደግሞ የአዉሮጳ ሕብረት ከአፍሪቃዉያን መንግሥታት ጋር ሳይነጋገርና የጋራ አቋም ሳይዝ ስደተኞችን የሚመለከቱ ርምጃዎችን ለመዉሰድ ማቀዱን ቀልድ በማለት ነቅፈዉታል።

Symbolbild Flüchtlinge Mittelmeer EU
ምስል Reuters/I. Zitouny

«የአዉሮጳዉ ሕብረት ባለዉ በዚህ ጉዳይ እጅግ አዝኛለሁ። እንደዉም መጀመርያ ላይ ልክ እንደቀልድ ብጤም ነዉ የተመለከትኩት። ይህ የስደተኞች ማዕበል እነዚህ ተገን ጠያቂዎች በተመድ ስለ ስደተኞች ጉዳይ በተደነገገዉን ነጥብ መሰረት ተሰዳጅ አይደሉም። እነዚህ ወደ አዉሮጳ ወደ ሸንጌን ሃገራት እያመሩ ያሉት ሰዎች፤ በሞሪታንያም ሆነ በሴኔጋል አግንቻቸዉ እንደነገሩኝ በትዉልድ ሃገራቸዉ ተስፋን ያጡ ወጣቶች ናቸዉ። አሁን ደግሞ እና እየተጫኑ የሚመጡበትን መርከብ እንናጥፋ እናዉድም እንላለን። እንዴት እንዲህ አይነት ሃሳብ ላይ መድረስ እንደተቻለ እኔ ግልፅ አልሆነልኝም። »
የአዉሮጳ ሕብረት ኮሚሽን የጀልባ ስደተኞችን ለመግታት ያወጣዉ መረሃ-ግብር ዋንና ርምጃ ይሆናል ብሎ ሳይሆን እገዛና ድጋፍ ይሰጣል ብሎ በመገመት መሆኑ ነዉ የተመለከተዉ እንድያም ሆኖ ሰዉ ያልጫኑ ጀልባዎችን እንዲሁም እነዚህ ጀልባዎች የሚመረቱበትን ቦታ ከማዉደም ይልቅ ሕገ-ወጥ ሰዉ አዘዋዋሪዎችን ተግባር ማስቆም አይቻልም ነበር? ለሚለዉ ጥያቄ የ«Grünhelme» ርዳታ ድርጅት ዋና ተጠሪ ሩፐርት ኖይዴክ ፤ ሃሳቡ ምንም የሚፈይደዉ ነገር የለም ባይ ናቸዉ።

«አዎ ሲሰሙት ጥሩ ይመስላል፣ በፖለቲካ ስራ ላይ ሲዉል ግን ምንም የሚፈይደዉ ነገር የለም። ምክንያቱም ከአዉሮጳ ሕብረት ኮሚሽን ፤ አልያም የየሃገራቱ መሪዎች የበርሊን ፖለቲከኞች ፤ ብሎም የኛ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፤ መራሂተ መንግስታችንም ቢሆኑ እንዲሁም የፈረንሳዩም ፕሪዚዳንት እስከ ዛሪ በመቶ ሽህ ስደተኞች ከሚፈልሱበት የሰሜን አፍሪቃን አልያም የምዕራብ አፍሪቃ የባህር ዳርቻ ሃገራት ጋር አልተነጋገሩም። አሁን ከአፍሪቃ ሃገራት መንግስታት ጋር መነጋገሩ ግድ ነዉ። በሃገራቱ የባህር ዳርቻ ወታደራዊ ጥቃትን በማካሄድ ችግሩን መቅረፍ አይገድም ብሎ መናገር ግን አይቻልም። ፖለቲካችን ትክክል ባለመሆኑ ሕገ- ወጥ ሰዎችን አዘዋዋሪዎቹ ከጊዜ ወደጊዜ እየተደራጁና እያካበቱ መጥተዋል»
የአዉሮጳ ሕብረት ኮሚሽን የስደተኝነት መንስኤዉና ሌሎች ጉዳዮች በሙሉ በጥብቅ መመርመር ወይም መታየት ይኖርበታል። ሰዎችን በሕገ ወጥ በሚያዘዋዉሩት ላይ ሊወሰድ የሚገባዉ ርምጃ በሚመለከት አስፈላጊ መሆኑ ተጠቅሶአል። እንደ ሩፐርት ኖይዴክ፤ ስለስደተኞች ጉዳይ እኛ በምናራምደዉ የተሳሳተ ፖለቲካ ሰዎችን በሕገ-ወጥ የሚያዛዉሩት እየተደራጁ እየሰፉ መተዋል ሲሉ ተናግረዋል።

« ሰዎችን በሕገ-ወጥ መንገድ የሚያዘዋዉሩት ሰዎች በምናራምደዉ የተሳሳተ የስደተኞች ጉዳይ ፖለቲካ ምክንያት እየተጠቀሙ እየተደራጁ ነዉ። በሞሪታንያ በሴኔጋል እንዲሁም በሌሎች ብዙ ሃገራት ያሉትን ተስፋ ያጡት አፍሪቃዉያኑ ስደተኞችን አዉቃቸዋለሁ፤ ፍላጎታቸዉ ለቤተሰቦቻቸዉን ለአካባቢያቸዉ ተስፋ ሰጭ ሆነዉ ለመርዳት እንዲሁም የሞያ ስልጠናና ሥራን ብቻ ነዉ ። እነዚህ ወጣቶች ከመጡበት በአንዱ በሁለተኛዉ ወይም በሶስተኛዉ ሃገር መንግስትን በማሳተፍ እነዚህ ወጣቶች ለኑሮዋቸዉ ተስፋ እንዲኖራቸዉና ወደ ሃገራቸዉ እንዲመለሱ ማድረግ ይቻላል። አሁን ግን ተስፋ ስለሌላቸዉ መመለስን አይሹም። እነዚህ ወጣቶች ከመጡበት አካባቢ ከ 1500 ዶላር በላይ ተበድረዉ ከወጡ በኋላ ገንዘቡን ከግማሽ በላይ አጥፍተዉታል። ይህን ገንዘብ ሳይዙ መመለስ ደግሞ አይችሉም። በኑሮአቸዉ ምንም አስተማማኝ ነገር አይኖራቸዉም።»

Mittelmeer Soldaten der Fregatte Hessen retten Flüchtlinge
ምስል picture-alliance/dpa/Bundeswehr/PAO/Mittelmeer
Mittelmeer Soldaten der Fregatte Hessen retten Flüchtlinge
ምስል Bundeswehr/PAO Mittelmeer/dpa

ስለዚህም እስካሁን ስለ ስደተኞች ጉዳይ የሠሩ የአዉሮጳ ሃገሮች ተስፋ በማጣት ወደ አዉሮጳ የሚሰደዱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣቶችን ለመርዳት ከሰሜን አፍሪቃ እንዲሁም ከሌሎች የአፍሪቃ ሃገሮች ጋር ግንኙነት በማድረግ በጥንካሪ የሆነ ነገር መሥራት ይኖርባቸዋል ሲሉ ሩፐርት ኖይዴክ ተናግረዋል።

ወደ አዉሮጳ ሃገራት የገቡ ስደተኞችን በኮታ ወደ ሕብረቱ አባል ሃገራት ማከፍፈል በሚለዉ ነጥብ ላይ የተለያዩ ሃገሮች ተቃዉሞ አሰምተዋል። ተቃዉሞዉን ካሰሙት ሃገሮች መካከል ፖላንድ ሃንጋሪና ብሪታንያ ይገኙበታል። ስለነዚህ ሃገራት አቋም ምን ይላሉ? « አዎ ይህን ጉዳይ ከነዚህ ሃገራት ጋር መስራት እንደማይቻል ከበፊቱምማወቅ ይቻል ነበር። እስካሁን ድረስ በአዉሮጳ ፖለቲካ እንደተደረገዉ ሁሉ ይህንን ለማድረግ ዝግጁ የሆኑ ሃገሮች መተባበር ይኖርባቸዋል።»

ሄክማን ዲክ ኦሊቨር
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ