1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለሕጻናት የተዘጋጀ የንባብ ጥግ

ዓርብ፣ ኅዳር 5 2007

ብሩክታይት ጥጋቡ አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኘው የ «ዊዝ ኪድስ ዎርክሾፕ» ድርጅት አጋር መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ ናት።

https://p.dw.com/p/1DmYd
Deutsche Schule in Äthiophien
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

ብሩክታይት ጥጋቡ ከ ዘጠኝ ዓመት በፊት ነበር ከአሜሪካዊው ባለቤቷ ሼን እተናሀውዘር ጋር «ዊዝ ኪድስ ዎርክሾፕ» የተባለውን ድርጅት የመሰረተችው። ብሩክታይት በሙያ መምህር ስትሆን ያለፉትን 9 ዓመታት ያሳለፈችው፤ ለህፃናት የሚሆኑ የመማሪያ መገልገያዎችን በማዘጋጀት ነው።

ይህው ድርጅት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ካቀረባቸው ስራዎች አንዱ በተለይ ኢትዮጵያ የሚኖሩ ህፃናት እና ወላጆች የሚያውቁት « ፀሀይ መማር ትወዳለች» የሚለው የህፃናት መማሪያ ዝግጅት ነው። ከዚህም ሌላ «ዊዝ ኪድስ ዎርክሾፕ» እድሜያቸው ከ10 በላይ ለሆኑ ታዳጊዎች «አሳትፉኝ» የሚል በፊልም የተዘጋጀ ፕሮግራም እንዳለው ብሩክታይት ገልፃልናለች። ሌላው ዝግጅት የአዳጊ ወጣቶች የሳይንስ ፍቅር እንዲያበረታታ የተቀረፀ፤ « ትንንሾቹ መርማሪዎች» የተባለው ነው። ከብሩክታይት ሥራ ለየት ያለው ግን ባለፈው ዓመት ድርጅቷ ለሕፃናት መስጠት የጀመረው « የንባብ ጥግ» የተባለ ፕሮግራም ላይ ይሆናል።የንባብ ጥጉ የተዘጋጀው ለሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሆን፤ ልጆቹን የሚያበረታታ መፅሀፍ እና ፊልም ከማዘጋጀት ባሻገር ለስራው ወሳኝ ስለነበረው ሂደት ብሩክታይት ጥቂቱን ጠርታልናለች።

Äthiopien Schulklasse in Bekoji
ምስል Getty Images

የ«ዊዝ ኪድስ ዎርክሾፕ» ድርጅት ስራዎችን በተለይ « የንባብ ጥግ» ብሎ ባለፈው ዓመት ለ20 የመንግሥት ትምህርት ቤት የ2ኛ ክፍል ተማሪዎች ያዘጋጀው ፕሮጀክት ላይ ነበር በዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት የተመለከትነው። ከድርጅትን አጋር መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ብሩክታይት ጥጋቡ ጋር የነበረንን ቆይታ በድምፅ ያገኙታል።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሀመድ