1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሁከት በፍራንክፉርት

ሐሙስ፣ መጋቢት 10 2007

የጀርመኗ ፍራንክፉርት ከተማ ትናት በዓመጽ ስትናጥ ነበር። መኪናዎች እና ጎማዎች አደባባዮች ላይ ሲነዱ፣ ቁሳቁሶች ሲወረወሩ የተቃውሞ ሰልፉ የተኪያሄደበት የከተማው ክፍልም በጥቁር ጢስ ተውጦ ታይቷል። የግጭቱ መንስዔ ደግሞ በፍራንክፉርት ከተማ አዲስ የአውሮጳ ማዕከላዊ ባንክ መከፈት ነው።

https://p.dw.com/p/1Eu92
ምስል picture-alliance/dpa/von Erichsen

የአውሮጳ ማዕከላዊ ባንክ መከፈት ነው። ባንኩ የኢምፔሪያሊስቶች መጠቀሚያ ነው በማለት የአውሮጳ የዕዳ ቀውስን የሚመለከተውን አሠራር ለመቃወም ቁጥራቸው ወደ 20,000 የሚጠጋ የተቃውሞ ሰልፈኞች አደባባይ ወጥተው ነበር። ለተቃውሞ የተጠራው የአደባባይ ሰልፍ ግን የተጠናቀቀው ተቃዋሚ ሰልፈኞች እና ፖሊሶችን ለግብግብ ቡጢ እና ቆመጥ ካስጨበጠ፣ ድንጋይ ካወራወረ፣ በርካቶችን ካስቆሰለ በኋላ ነበር። በግጭቱ 200 በላይ ሰልፈኞች እንዲሁም 150 ፖሊሶች መቁሰላቸው ተነግሯል። እንደ ፖሊስ ዘገባ ከሆነ 26 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። የፍራንክፉርቱ ወኪላችን ጎይቶም ቢሆን ትናንት ሔሊኮፕተር በሰልፈኞቹ አናት ሲያንዣብብ፣ የፖሊስ መኪና በእሳት ሲያያዝ ሰልፉ በተኪያሄደበት ቦታ ተገኝቶ ነበር።

ተክሌ የኋላ

ጎይቶም ቢሆን

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ