መሃይምነትን ለማስወገድ ያለመዉ የጎልማሶች የትምህርት ቀን በዓለም ደረጃ ዛሬ ታስቦ ዉሏል።
በኢትዮጵያም በኦሮሚያ ፍቼ ዞን በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል። በ21ኛዉ ክፍለ ዘመን የመጀመሪያ አስርት ዓመታት ከ754 ሚሊዮን ያልተማረዉ የዓለም ህዝብ ከሶስቱ ሁለቱ ሴቶች መሆናቸዉ ተመልክቷል።
ታደሰ እንግዳዉ፤ ሸዋዬ ለገሠ
ተክሌ የኋላ
በይግባኝ ባይ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤና በመልስ ሰጪ ተከሳሽ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ማኅበራት ኤጀንሲ መሃል የተጀመረዉን ክርክር ዛሬ ለዉሳኔ የቀጠረዉ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፤ ሰበር ሰሚ ችሎት ዉሳኔዉን ለሌላ ቀን ቀጠረ።
በአሜሪካን የሚኖሩ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አባላት፤ ዓለም ዓቀፉ የክርስቲያኖች መብት ተሟጋች ተቋምና ዓለም ዓቀፉ የመብት ተሟጋች ሂዉማን ናይትስ ዎች ታሳሪዎቹን ለማስፈታት የየበኩላቸዉን ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ። በተለይ በሴቶቹ ታሳሪዎች ላይ ከፍተኛ የፆታ ጥቃት መፈጸሙ ተገልጿል።