የዓለም የምግብና ግብርና ድርጅት በአዉሮጳዉያኑ 2007ዓ,ም ይፋ ባደረገዉ ዘገባ ኢትዮጵያ የደን ይዞታቸዉ እየተመናመነ ከሚገኙ አገራት ከመጨረሻ በአምስተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ጠቁሟል።
በዚህ ዘገባ መሠረት ኢትዮጵያ የቀደመቻቸዉ አገራት ከሰሃራ በረሃ ዳር ላይ የሚገኙትና ተፅዕኖዉ የሚያጠቃቸዉ እንደነማሊ፤ ኒዠርና ሞሪታንያ የመሳሰሉት አገራት ናቸዉ። ጥናቶች በተደጋጋሚ እንዳመለከቱትም ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የደን ይዞታቸዉ አሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኝ አገራት ከጥቂት አስርት ዓመታት በኋላ የደን ሃብታቸዉ ጨርሶ ሊጠፋ ይችላል የሚል ነዉ።
ሸዋዬ ለገሠ፤
ሂሩት መለሠ