በዓለማችን በአንድ ቀን ዉስጥ 8,000 ታዳጊ ሴቶች ግርዛት ይፈጸምባቸዋል። በተመሳሳይ በየአስራ አንድ ሰከንዱ ደግሞ አንዷ ልጅ የዚህ ጎጂ ልማድ ሰለባ ትሆናለች።
ጎጂ ልማዱ የጠናባት የሶማሊያ ሴቶች
በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በሴት ልጆች ላይ የሚፈፀመዉን ይህን ጎጂ ባህላዊ ልማድ ለማስቆም የተጀመረዉ እንቅስቃሴ ፍሬ እያሳየ ቢሆንም ዛሬም ብዙ ሊሰራ እንደሚገባ እየተነገረ ነዉ። የሴትልጅ ግርዛት ይቁም የተሰኘዉን ዘመቻ ያዘከረዉ ዓመታዊ ዕለት ባሳለፍነዉ ሳምንት መጨረሻ ታስቧል። ዘመቻዉ በሴቶች ብቻ ሳይሆን የወንዶችንም ትብብር እንደሚሻ ነዉ የተነገረዉ።
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ