የዛሬ ሁለት ሳምንት ከሊባኖስ ቤይሩት ወደአዲስ አበባ በረራ ወጥኖ ከመነሻዉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዉሮፕላን በአየር ላይ ተበታትኖ ከሜዲትራኒያን ባህር መዉደቁ ይታወሳል።
የቤይሩት አዉሮፕላን ማረፊያ
የበረራ ቁጥር 409 አዉሮፕላን ለገጠመዉ አደጋ ያበቃዉ ምክንያት እስካሁን አልታወቀም። ያን ለማወቅ ከሚረዱ የበረራ መረጃ መመዝገቢያ ቁሳቁስ መካከል ሁለቱ መገኘቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቴክኒክ አገልግሎት መምሪያ ሃለፊ ና የዚህ አደጋ መረጃ ተከታታይ ግብረሃይል የበላይ ካፒቴን ደርስታ ዘርዑ ዛሬ ለዶቼ ቬለ አረጋግጠዋል።
ሸዋዬ ለገሠ
ተክሌ የኋላ