ኢትዮጵያ ውስጥ ዝናም ወቅቱን አልጠብቅ ብሏል። አንዳንዴ ጀምሮ ያቋርጣል፣ መጠኑም ቢሆን እየቀነሰ መምጣቱ እየተስተዋለ ነው።
በግብጽ - የአስዋን ግድብ
ዝናም ወቅቱን ጠብቆ አልመጣ በማለቱ፣ ቢመጣም መጠኑ በቂ ባለመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ በየጊዜው እያስከተለ ስላለው ችግርና በሳቴላይት አማካኝነት የአየር ንብረት ለውጥን ለማወቅ ስለሚደረገው ምርምር ፤ በዚህ ዙሪያ ጥናት ካደረጉትና አሁንም ትምህርታቸውን በከፍተኛ ደረጃ በበርሊን ዩኒቨርስቲ በመከታተል ላይ ከሚገኙት ፣ከአቶ ኤፍሬም ገብረማርያም ጋር ባለፈው ሳምንት ተነጋግረን እንደነበረ የሚታወስ ነው። በዛሬው ሁለተኛና የመጨረሻ ክፍል ቃለ-ምልልሳችን ፣ በአማራጭ መፍትኄዎች ዙሪያ ይሆናል የምናተኩረው።
ተክሌ የኋላ/አርያም ተክሌ