1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የቡሄ በአል

ቡሄ መጣ ያ መላጣ ቅቤ ቀቡት እንዳይነጣ ቡሄ በሉ ልጆች ሁሉ እያልን ሆ ስንል ከዋቂዎች ስጦታን ስናገኝ ደስታችን ልዩ ነዉ

ኢትዮጽያዉያን ህጻናት በፍራንክፈርት በኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን በክበረ በአል ላይ

የቡሄ በአል የክረምቱ ማለቅያ ነሃሴ አስራ ሁለት አስራ ሶስት አካባቢ ሲከበር ቡሄ ካለፈ የለም ክረምት ዶሮ ከጮኸ የለም ለሊት ይባላል። የቡሄ በአል ካለፈ በኻላ መስከረም ስለሚጠባ እና ብራ ስለሚሆን። ደስታ ተክለወልድ በጻፉት መዝገበ ቃላት ህጻናት በቡሄ እለት ሆ ብለዉ ዳቦ ለሰጣቸዉ ምስጋና ሲያቀርቡ የሚሉትን አስፍረዋል
ሃሚና ሃሚና
ዘነዘና የብር ዘነዘና
ጌታዪን ያማ ሰዉ
ነጭ እከክ ይዉረሰዉ!

ስለቡሄ አዋቂዎችን ጥይቀን፣ ሆያ ሆዪ ብለናል ያድምጡን

Audios and videos on the topic