1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀድሞዉ ፕሬዝዳንት የመታከሚያ ችግር

ማክሰኞ፣ ሰኔ 26 2004

ለአስራ-ስምንት ዓመታት ላበረከቱት አገልግሎት የሚከፈላቸዉ ጡረታ በወር አንድ-ሺሕ ሰወስት መቶ ብር ነዉ።ዶክተር ነጋሶ እንደሚሉት በጣም የሚያሳዝናቸዉ ግን በቅርቡ በተቃዋሚ ፖለቲከኞችና ጋዜጦች ላይ የተላለፈዉ ብይን ነዉ።

https://p.dw.com/p/15QaJ
Autor: Ludger Schadomsky Copyright: Ludger Schadomsky/DW Titel: Dr. Negasso Gidada Thema: Der ehemalige Staatspräsident und heutige Vize-Vorsitzender des Achtparteien-Oppositionsbündnisses „Medrek“ , Dr. Negasso Gidada, ist vor der Wahl ein gefragter Gesprächspartner Schlagwörter: Negasso Gidada, Medrek, Forum, Äthiopien 2010, Äthiopien Opposition, Ethiopia 2010, Wahl Äthiopien
ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳምስል DW

የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ፕሬዝዳት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ሁለት እግሮቻቸዉን የሚያሳጣ በሽታን ለመታከም በቂ ገንዘብ አጥተዉ ለመበደር መገደዳቸዉን አስታወቁ።ባሁኑ ጊዜ ጀርመን የሚገኙት የተቃዋሚዉ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ መሪ ዶክተር ነጋሶ እንደገለፁት ለሕክምና የሚያስፈልጋቸዉ አስር ሺሕ ዩሮ ግድም ነዉ።ዶክተር ነጋሶ ሥልጣናቸዉን ለቀዉ ከኢሕዲግ መንግሥት እስከወጡበት ጊዜ ድረስ የማስታወቂያ ሚንስትር፥ የሕገ-መንግሥት አፅዳቂ ኮሚሽን ሊቀመንበርና የኢትዮጵያ ፕሬዝዳት ሆነዉ አገልግለዋል።ተቃዋሚዉን ፓርቲ ከመቀላቀላቸዉ በፊት ደግሞ በግል የምክር ቤት እንደራሴ ሆነዉ ሠርተዋል።ለአስራ-ስምንት ዓመታት ላበረከቱት አገልግሎት የሚከፈላቸዉ ጡረታ በወር አንድ-ሺሕ ሰወስት መቶ ብር ነዉ።ዶክተር ነጋሶ እንደሚሉት በጣም የሚያሳዝናቸዉ ግን በቅርቡ በተቃዋሚ ፖለቲከኞችና ጋዜጦች ላይ የተላለፈዉ ብይን ነዉ።የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤል ዶክተር ነጋሶን አነጋግራቸዋል።

ይልማ ሐይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ