ወጣት አርቲስት ጎሳዬ ቀለሙ(ጃኪ) ስለ ራሱ እና ስራዎቹ ከዶይቸ ቬለ ጋ ቆይታ አድርጓል። በተለያዩ የአውሮፓ አገራት እየተዟዟረ ስራዎቹን አሳይቷል አሁንም እያሳየ ይገኛል። በአሁኑ ሰዓት ከሚኖርበት ኔዘርላንድስ ሄዶ በአዲስ አበበ ይገኛል። አዲስ ዘፈኖቹን እየቀረፀ ከሚገኝበት እስቱዲዮ ሆኖ ከልደት አበበ ጋ ተነጋግሯል።
ልደት አበበ
አርያም ተክሌ
«ትምህርት ደበረኝ። ወላጆቼ ጣጣ ያበዙብኛል፣ እኔ ህፃን አይደለሁም » እነዚህ አረፍተ ነገሮች በአብዛኞቹ በአፍላ የእድሜ ክልል ውስጥ ባሉ ታዳጊ ወጣቶች አንደበት አዘውትረው ይደመጣሉ።