1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ድሬዳዋ 56 ቋሚ ቅርሶችን አስመዘገበች

ዓርብ፣ ነሐሴ 26 2015

የድሬዳዋ የከተማዋ አስተዳደር ቋሚ ቅርሶች እውቅና እንዲያገኙ ሲያደርጉት በነበረ ጥረት ለእውቅና በቅተዋል ከተባሉ ሃምሳ ስድስት ቅርሶች መካከል ከአንድ መቶ አመት እድሜ በላይ ያስቆጠረው በቀድሞው አጠራር የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ድርጅትን ጨምሮ ረዥም እድሜ ያስቆጠሩ አብያተ ክርስትያናት እና መስኪዶች ፣ ኪነ ህንፃዎች እና ሌሎችም ይገኙበታል።

https://p.dw.com/p/4VrEI
Äthiopien Dire Dawa City
ምስል DW/Y. Gebreegziabher

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከ50 በላይ ቋሚ ቅርሶችን አስመዘገበ

ድሬደዋ አሉኝ ከምትላቸው ቋሚ የቅርስ ሀብቶች ሃምሳ ስድስት ያህል ለሚሆኑት እውቅና መስጠቱን የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል። የድሬደዋ መስተዳድር የባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት ከባለስልጣን መ/ቤቱ ጋር የከተማይቱን ቋሚ ቅርሶች እውቅና እንዲያገኙ ሲያደርጉት በነበረ ጥረት ለእውቅና በቅተዋል ከተባሉ ሃምሳ ስድስት ቅርሶች መካከል ከአንድ መቶ አመት እድሜ በላይ ያስቆጠረው በቀድሞው አጠራር የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ድርጅትን ጨምሮ ረዥም እድሜ ያስቆጠሩ አብያተ ክርስትያናት እና መስኪዶች ፣ ኪነ ህንፃዎች እና ሌሎችም ይገኙበታል።

ድሬደዋ አሉኝ ከምትላቸው ቋሚ የቅርስ ሀብቶች ሃምሳ ስድስት ያህል ለሚሆኑት እውቅና መስጠቱን የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን አስታውቋል።
ለእውቅና በቅተዋል ከተባሉ ሃምሳ ስድስት ቅርሶች መካከል ከአንድ መቶ አመት እድሜ በላይ ያስቆጠረው በቀድሞው አጠራር የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ድርጅትን ጨምሮ ረዥም እድሜ ያስቆጠሩ አብያተ ክርስትያናት እና መስኪዶች ፣ ኪነ ህንፃዎች እና ሌሎችም ይገኙበታል።ምስል Mesay Teklu/DW

የኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ህይወት ኃይሉ በድሬዳዋ በተካሄደ መድረክ እንዳሉት ባለፉት አመታት በመስተዳድሩ ለእውቅና ምዝገባ ከቀረቡ ቋሚ ቅርሶች ሃምሳ ስድስት ያህሉ እውቅና አግኝተዋል።የኩላሊት እጥበት የህክምና ማዕከል በድሪዳዋ

ባለስልጣኑ በድሬደዋ የሚገኙ ቋሚ ቅርሶችን ለመመዝገብ በተንቀሳቀሰባቸው ጊዜያት በመልካም ሁኔታ ላይ ያሉ ቅርሶች እንደመኖራቸው ሁሉ በመልሶ ማልማት እና እድሳት እጦት ስጋት የተጋረጠባቸው እንዳሉ መገንዘባቸውን የጠቀሱት ኃላፊዋ አስፈላጊው ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

በመልሶ ማልማት እና እድሳት እጦት ስጋት የተጋረጠባቸው እንዳሉ መገንዘባቸውን የጠቀሱት ኃላፊዋ አስፈላጊው ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቀዋል።
የኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ህይወት ኃይሉ በድሬዳዋ በተካሄደ መድረክ እንዳሉት ባለፉት አመታት በመስተዳድሩ ለእውቅና ምዝገባ ከቀረቡ ቋሚ ቅርሶች ሃምሳ ስድስት ያህሉ እውቅና አግኝተዋል።ምስል Mesay Teklu/DW

በመድረኩ የተገኙት የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በመስተዳድሩ ለሚገኙ ቋሚ ቅርሶች ተገቢው እውቅና መሰጠቱ ያለውን ጠቀሜታ ከመግለፅ ባሻገር ቅርሶቹ ለታሪክ እና ለትውልድ እንዲሻገሩ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ አስረድተዋል።የበረራ አደጋ ምላሽ ሰጪ ተቋማት

በመድረኩ እውቅና ካገኙ ቋሚ ቅርሶች መካከል አንዱ የሆነው የቀድሞው ኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር በአዲሱ መጠርያው የድሬደዋ ደወሌ ባቡር ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ አየለ ወልደ ዮሃንስ እውቅናው ጠቃሚ መሆኑን በማንሳት በተለይም ድርጅቱ በአዲስ መልክ በቱሪዝም ዘርፍ ለጀመራቸው ስራዎች አጋዥ ነው ብለዋል።

ትናንት በድሬደዋ በተካሄደው የእውቅና አሰጣጥ መድረክ ቋሚ ቅርሶችን ጠብቀው በማቆየት ምስጉን ተግባር የፈፀሙ የእምነት ተቋማት እና ድርጅቶች እውቅናውን ተቀብለዋል።

ትናንት በድሬደዋ በተካሄደው የእውቅና አሰጣጥ መድረክ ቋሚ ቅርሶችን ጠብቀው በማቆየት ምስጉን ተግባር የፈፀሙ የእምነት ተቋማት እና ድርጅቶች እውቅናውን ተቀብለዋል።
የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በመስተዳድሩ ለሚገኙ ቋሚ ቅርሶች ተገቢው እውቅና መሰጠቱ ያለውን ጠቀሜታ ከመግለፅ ባሻገር ቅርሶቹ ለታሪክ እና ለትውልድ እንዲሻገሩ አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ አስረድተዋል።ምስል Mesay Teklu/DW

የእንቁፍቱ ዋሻ 

በትናንትናው የቋሚ ቅርሶች እውቅና መርሀ ግብር እውቅና ያገኘው የእንቁፍቱ ዋሻ በከተማው ቀበሌ የሚገኝ ሲሆን ባለስልጣኑ ባደረገው ድጋፍ ዋሻውን በአጥር የመከለል ስራ ተሰርቶለታል። 

የድሬደዋ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሚካኤል እንዳለ ዋሻው በውስጡ የሮም አርቶች ፣ የድንጋይ ላይ ምስሎች እንዲሁም በርካታ መጓጓዣ አቅጣጫዎች እንዳሉት ተናግረዋል።የድሬዳዋ የሪፈረንደም ጉዳይ እያወዛገበ ነው

ዋሻውን አልምቶ ለመስህብነት ለማዋል ከሚደረገው ጥበቃ እባ እንክብካቤ በተጨማሪ የዘርፉ ባለሞያዎች ጥናት ምርምር የሚያደርጉበት ሁኔታ ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

መሳይ ተክሉ 

ታምራት ዲንሳ

ነጋሽ መሐመድ