1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦሮሚያው ግጭት እና የሰላማዊ ሰዎች አበሳ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 15 2016

መረጃውን ያጋራው ግለሰብ የቤተሰባቸው አባል የሚገኙበት ዘጠን ሰዎች በምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ ወሻ እና ቡቢሳ በተባሉ ቀበሌያት ተገድለው ተጥለው ቢገኙም አንስተው ለመቅበር እንኳ እድሉን መነፈጋቸውን ጠቅሰው ለማን እንንገር በማለት አስተያየታቸውን በሀዘን አጋርተዋል፡፡

https://p.dw.com/p/4f63V
በአርሲ ዞን ሰላማዊ ሰዎች እየታገደሉ መገደላቸዉ አሁንም እንደቀጠለ ነዉ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መስተዳድር ከአርሲ ዞን ቀበሌዎች አንዱምስል Seyoum Getu/DW

የኦሮሚያው ግጭት እና የሰላማዊ ሰዎች አበሳ


በምዕራብ አርሲ ዞን ከአዳባ ከተማ ባለፈዉ ሳምንት ታግተዉ ተገደሉ የተባሉ ሰዎችን አስክሬን እግኝተዉ አግኝተው ለመቅበር መቸገራቸዉን የሟች ቤተሰቦች አስታወቁ።በኦሮሚያ ክልል በቀጠለዉ ግጭትና ሥርዓተ አልበኝነት  ሰላማዊ ሰዎች በየጊዜዉ እየተገደሉ ነዉ።ይሕ በንዲሕ እንዳለ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ከሰሞኑ በድጋሚ የሰላም ጥሪን ለታጣቂዎች አስተላልፈዋል፡፡

የአዳባ ዙሪያው ግድያ ምንነት

ከሰሞኑ “ዘመዶቼ የቤተሰቤ አባላት ተገድለው አምስት ቀናት ብያልፋቸውም መቅበር አልቻልኩም” በሚል በማህበራዊ መገናኛ ዘዴ የተጋራው መረጃ የበርካቶች መነጋገሪያ የሆነና ብዙውዎች የተጋሩት ነበር፡፡ መረጃውን ያጋራው ግለሰብ የቤተሰባቸው አባል የሚገኙበት ዘጠን ሰዎች በምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳወሻ እና ቡቢሳ በተባሉ ቀበሌያት ተገድለው ተጥለው ቢገኙም አንስተው ለመቅበር እንኳ እድሉን መነፈጋቸውን ጠቅሰው ለማን እንንገር በማለት አስተያየታቸውን በሀዘን አጋርተዋል፡፡
ዶቼ ቬለ ከአዳባ በስልክ ያነጋገራቸው ከነዚህ ተገደሉ ከተባሉ ሰዎች የሶስቱ ቤተሰብ የቅርብ ዘመድ ነን ያሉ አስተያየት ሰጪ ሱዲ ሀጂ ዋቆ፣ አብዱልከሪም አቡበከር (ጃዋሮ ሰዴ) እና ሩቂያ ሰዴ የተባሉ የአንድ ቤተሰብ አባላት ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ከሰዓት 10 ሰዓት አከባቢ ከአዳባ ከተማ አስፋልት መንገድ ዳር ተወስደው በማግስቱ አስከሬናቸው በተለያዩ የአከባቢው ገጠር ቀበሌያት ተጥሎ መገኘቱን አስረድተዋል፡፡ 
“ሶስት የተገደሉብን ቤተሰቦቸቻችን አብዱልከሪም አቡበከር፣ ሩቂያ ሰዴ እና ሱዲ ሀጂ ናቸው፡፡ ሩቂያ ሴት ስትሆን ሁለቱ ወንዶች ናቸው፡፡ ከገቢያ ቦታ ስመለሱ ነበር ተወስደው የተገደሉት፡፡ አሁን አስከሬን አንስተን ለመቅበር አይደለም ሀዘን እንኳ እድንቀመጥ አልተፈቀደልንም፡፡ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ የተወሰዱት የኛ ቤተሰብ እነዚህ ናቸው፡፡ ሌሎች በተጨማሪነት የተገደሉ እንዳሉ በመረጃ ደረጃ እንሰማለን፡፡ የተፈጸመውን እያንዳንዱን ነገር እንደቤተሰብ ለማወቅ ተቸግረናል፡፡ ግን በእለቱ የጸጥታ አካላት ወደ ወረዳ ቢሮ እንደወሰዳቸው ያው ከተማው በሙሉ ተመልክቷል፡፡ እዚያ ሄደን ስንጠይቅ ግን እንዲህ የሚባሉ ሰዎችን አናውቅም እዚህም አልመጡም ይሉናል፡፡ ሄደን አስከሬን ለማንሳት ብንቸገርም አስከሬናቸው ወሻ በሚባል ተራራ፣ በቡቻ ቀበሌ እና ቡቢሳ በሚባል ቀበሌ በተለያዩ ሶስት ቦታዎች ተገድለው መገኘታቸውን ከሰው ብቻ ሰምተናል” ብለዋል፡፡
ለአስተያየት ሰጪው በተጨማሪነት ላቀረብነው ጥያቄ ምላሽ ስሰጡ እነዚህ ሶስት የቤተሰቦቻቸው አባላት የተገደሉት መንግስት ‘ሸነ’ ያለውና እራሱን ‘የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት’ ብሎ የሚጠራውን የታጠቀ አማጺ ቡድንን በመቀለብ እና ድጋፍ በመስጠት ተጠርጥረው እንደሆነ እንደሚያውቁ አስረድተዋል፡፡ ለደህንነታቸው እጅጉን አሰድጊ ያሉት ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን ያስረዱት እኚህ አስተያየት ሰጪ ቤተሰብ እስካሁን የተቀመጠ ሀዘንም የለም ነው ያሉት፡፡
የዚህ ቤተሰብ አባል መሆናቸውን ገልጸው አስተያየታቸውን ያጋሩን ሌላኛዋ የቤተሰብ አባል ሰላማዊ ያሏቸውን እነዚህን የተገደሉ የቤተሰቦቻቸው አባላት ከሻሸመኔ ከትምህርት መልስ ቤተሰብ ጥየቃ የመጣ እንደምገኝበትም ተናግረዋል፡፡ ከተገደሉት ሶስቱ ሰዎች አንዱ ወንድማቸው፤ ሎሎች ሁለቱ ደግሞ አክስት እና አጎታቸው መሆናቸውን አስረድተው “ይህ ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች ላይ የተቃጣ ጥቃት ነው፡፡ ሻሸመኔ ኮሌጅ የሚማር ልጅ ለበኣል እንደመጣ በዚህ ውስጥ ሰለባ የሆነ አለ፡፡ ሱዲ ሀጂ የተባሉ ደግሞ ለስራ ዶዶላ ውለው ነበር የተመለሱት፡፡ ሩቂያ ሰዴ አክስቴ ናት አሳድጋኛለች፡፡ ማክሰኞ 10 ሰኣት አከባቢ ከቤት እንደወጡ በማግስቱ አስከሬናቸው መገኘቱን ነው የሰማነው፡፡ አስከሬናቸው በተለያዩ አከባቢዎች መጣሉን በወሬ ደረጃ ብንሰማም ሄደን አንስተን ለመቅበር ለህይወታችን ሰግተናል፡፡ ሀዘናችንም ለመግለጽ አልቻልንም” ብለዋል፡፡

የሟች ቤተሰቦች እንደሚሉት የተገደሉ ዘመዶቻቸዉን አስከሬን እንኳ መቅበር አልቻሉም
በአርሲ ዞን በተለይ ከአዳባ ከተማ ታግተዉ የተወሰዱ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸዉ እየተነገረ ነዉምስል Seyoum Getu/DW

ስለግድያ የመንግስት ባለስልጣናት አስተያየት

በዚህ አከባቢ ተፈጸመ ስለተባለው ግድያ ለማጣራትና ተጨማሪ መረጃዎችን ለማጠየቅ ዶይቼ ቬለ ለወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ብደውልም ስብሰባ ላይ ነኝ በማለታቸው አስተያየታቸው ማካተት አልተቻለም፡፡ የዞኑ ጸጥታ ዘርፍ አስተዳዳሪ አቶ ያሲን ገርጁም ስለሁኔታው ተጠይቀው በዚያ የተገደለ ሰላማዊ ሰው አላውቅም ሲሉ በአጭር መልሰዋል፡፡ ስለዚህ ግድያ በተናጥል በክልሉ መንግስትም ሆነ በሰብዓዊ ተቋማት እስካሁን የተባለ ነገር የለም፡፡ በርግጥ ከዚህ በፊት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ጊዜያት ያለፍርድ ሰዎች እንደሚገደሉ በተደጋጋሚ ባወጣው መግለጫ መግለጹ ይታወሳል፡፡ 
በኦሮሚያ ባላቧራው ግጭት መዘዝ በተለያዩ አከባቢዎችበተፋላሚዎች መካከል በሚደረግ ፍልሚያ ሰላማዊ ሰዎች ጭምር ይገደላሉ፡፡ 
ከሰሞኑ ደግሞ የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ሽመለስ አብዲሳ በይፋዊ ማህበራዊ ገጻቸው ባሰፈሩት ዘለግ ያለ ጽሁፍ በክልሉ ሰላም ለማስፈን እየተጉ መሆኑን፤ መንግስታቸው “እየተመለሱ ያሉ” ያሏቸውን ታጣቂዎች በይቅርታ እና በደስታ እየተቀበሉዋቸው መሆኑን ገልጸው፤ ሌሎችም ለሰላማዊ ውይይት እንዲቀመጡ ጠይቀዋል፡፡
በኦሮሚያ ለአምስት ዓመታት ያለማቋረጥ ሲካሄድ ለነበረው ግጭት ጦርነት እልባት ለመስጠት በሶስተኛ ወገኝ አሸማጋይነት ጭምር የተደረገው ተከታታይ ጥረት የተጠበቀውን ውጤት ሳያስገኝ መቅረቱ አይዘነጋም፡፡

ሥዩም ጌቱ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ