ኤኮኖሚኢትዮጵያየኢትዮጵያ ገበያ ለውጭ ባለወረቶች ሲፈቀድ ባለሙያዎች ተስፋ እና ሥጋት ተሰምቷቸዋልTo play this audio please enable JavaScript, and consider upgrading to a web browser that supports HTML5 videoኤኮኖሚኢትዮጵያEshete Bekele/MMT9 ሚያዝያ 2016ረቡዕ፣ ሚያዝያ 9 2016ለኢትዮጵያውያን ተከልለው የቆዩ የወጪ እና ገቢ ንግድ ሥራዎች ለውጭ ባለወረቶች ተፈቅደዋል። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ መመሪያ የውጭ ባለወረቶች በጅምላ እና ችርቻሮ ንግድ ዘርፎች ጭምር እንዲሳተፉ የፈቀደ ነው። መንግሥት ለረዥም ዓመታት ሲከተል በቆየው ፖሊሲ ረገድ ያደርገው ለውጥ ለአንዳንድ ባለሙያዎች ተስፋ ለሌሎች ሥጋት ያጫረ ሆኗል። https://p.dw.com/p/4etYQማስታወቂያ