1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ምዕምናን ሰልፍ በፍራንክፈርት

ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 12 2016

በጀርመን የሚኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ምዕምናን ፍራንክፈርት ከተማ ሰልፍ አካሔዱ። በተለያዩ የጀርመን ከተሞች የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት አባቶች እና ምዕምናን መሳተፋቸውን በጀርመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ካሕናት መራዊ ተበጀ ለዶይቼ ቬለ አስረድተዋል።

https://p.dw.com/p/4f0Qt
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ምዕምናን ሰልፍ በፍራንክፈርት
በተለያዩ የጀርመን ከተሞች የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት አባቶች እና ምዕምናን መሳተፋቸውን በጀርመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ካሕናት መራዊ ተበጀ ለዶይቼ ቬለ አስረድተዋል።ምስል Privat

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ምዕምናን ሰልፍ በፍራንክፈርት

በጀርመን የሚኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ምዕምናን በፍራንክፈርት ከተማ ሰልፍ አካሔዱ። የሰልፍ ጥሪ የተላለፈው በጀርመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሀገረ ስብከት ስም ነው። በተለያዩ የጀርመን ከተሞች የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት አባቶች እና ምዕምናን መሳተፋቸውን በጀርመን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ካሕናት መራዊ ተበጀ ለዶይቼ ቬለ አስረድተዋል።

 በጀርመን የኢኦተቤ/ክርስቲያን ምሥረታ 40ኛ ዓመት

በኢትዮጵያ በተለይ ባለፉት “ስድስት ዓመታት ውስጥ የተደረገው ግፍ፣ ሰቆቃ፣ ጩኸት፣ የገዳማት መደፈር፣ የመናንያን መነኮሳት መሞት፣ የሕዝቦች መፈናቀል፣ በሀገሪቱ ላይ የሚደርሰው እና የሚታየው ቀውስ ሁሉ” ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንዳስገደዳቸው ሊቀ ካሕናት መራዊ ተበጀ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

ሊቀ ካሕናት መራዊ ተበጀ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ውስጥ በሚገኘው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የተፈጸመውን የመነኮሳት ግድያ በምሳሌነት ጠቅሰዋል።

“በደብረ ኤልያስ የተደረገው፣ በሌሎቹም ቦታዎች የተደረገው ጥፋት እና እልቂት እጅግ እያስቆጨን፣ እጅግም እያናደደን፣ ብሶታችንም ከለት ወደ ዕለት እየበዛ፣ እየከፋ በመሔዱ እነሆ ድምጻችንን እናሰማለን” ሲሉ ተናግረዋል። 

ዛሬ ቅዳሜ ቀትር ሰልፉ እየተካሔደ በሚገኝበት ወቅት ሊቃ ካሕናት መራዊ ተበጀን በስልክ አነጋግሪያቸዋለሁ። 

ቃለ ምልልሱን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ 

እሸቴ በቀለ