1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የመጠጥ ውኃ ችግር በኢትዮጵያ

ሐሙስ፣ ግንቦት 3 2015

በኢትዮጵያ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ችግር ዘላቂ መፍትኄ አልተበጀለትም ። በተለይ ከተሞች እየሰፉ የሕዝብ ብዛቱ እየጨመረ በመጣባቸው አካባቢዎች ችግሩ የከፋ ነው። ለሰው ልጅ እጅግ አንገብጋቢ እና አላቂው የውኃ ሀብት በአግባቡ ለመጠቀምና እኩል ተደራሽ ለማድረግ ደግሞ መንግስት የግል ባለሀብቶችን ማሳተፍ ይኖርበታል ሲሉ የዘርፉ ባለሞያዎች ይናገራሉ ።

https://p.dw.com/p/4RDoF
Symbolbild | Wasser
ምስል Anton Eine/PantherMedia

በተለያዩ ቦታዎች ችግሩ የከፋ ነው

በኢትዮጵያ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት ችግር ዘላቂ መፍትኄ አልተበጀለትም ። በተለይ ከተሞች እየሰፉ የሕዝብ ብዛቱ እየጨመረ በመጣባቸው አካባቢዎች ችግሩ የከፋ ነው። ለሰው ልጅ እጅግ አንገብጋቢ የሆነውን አላቂ የውኃ ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም እና እኩል ተደራሽ ለማድረግ ደግሞ መንግስት የግል ባለሀብቶችን ማሳተፍ ይኖርበታል ሲሉ የዘርፉ ባለሞያዎች ይናገራሉ ።

በዋና ከተማዋ አዲስ አበባ ያሉ ነዋሪዎች ውኃ ለማግኘት ሳምንት ዐሥራ አምስት ቀን ከፍ ሲል 20 እና 25  ቀን  የሚጠብቁ  ቦታዎች ጥቂት አይደሉም  የንጹህ ውኃ ችግር ወቅት ሳይገድበው  ከክረምት እስከ በጋ ተመሳሳስይ ነው ። ይህንን ስር የሰደደ ችግር ለመፍታት መንግስት የግል ባለሀብቶችን ካላሳተፍ በስተቀር  ሁኔታው በቀላሉ መፍትሄ ሊይገኝለት የሚችል አደለም ።  መንግስት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ባሰበው እና በፈለገው መልኩ እንዲያድግ ውሀ መሰረታዊ ነው ያለንን ውሀ ያለ አግባብ  ሳናባክን መጠቀም   ይኖርብናል ። ወደሀገር ውስጥ ለኢንቨስትመንት የሚገቡ የውጭ ባለሀብቶች  ዓለምአቀፍ  የውኃን ስምምነት እና ሕግጋትን  እንዲያከብሩ እና እንዲተገብሩ መደርግ አለበት ያሉት DW  ያነጋገራቸው የከርሰምድር ባለሞያ መንግስት በዚህ ዘርፍ ያሉትን ሀሳቦች ለማስተናገድ ጠጠረጴዛውን ክፍት ማድረግ አለበት ሲሉ ለ DW ተናግረዋል ። መንግስት መሬት እና ርካሽ የሰው ኃይል ከመቅረቡ ባሽገር ያካባቢውን ውኃ ባግባቡ እና በኃላፊነ የሚጠቁብት ብሎም ሥራ በሚሰሩበት አካባቢ ላለው ማኅበረሰብ ንፁሕ የውኃ አአቅርቦት ላይ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ የሚያስችል ፓሊሲዎች ተቀርፀው ሥራ ላይ መዋል ይኖርባቸዋል በተለይ የሀገራችን ባለሀብቶች ወሀን አጣርቶ በጠርሙስ አለያም በፖፕላስቲክ መያዣዎች አሽጎ ከመሽጥ ባለፈ ውኃን በ እንክብካቤ እና ብክነትን በመቀነስ ሥራ እንዲሳተፉ የሚደረግ   ፖሊሲ መቅረፅ አለበት ሲሉ ለ DW የተናገሩት ።

አእዋፋት ውኃ ሲጠጡ፦ ምስል ከክምችት ክፍል
አእዋፋት ውኃ ሲጠጡ፦ ምስል ከክምችት ክፍልምስል Frank Rumpenhorst/dpa/picture alliance

ምንም እንኩዋን ሀገራችን በቂ ወንዝች እና የክረምት ወኃ ቢኖራትም ያለውን ውኃ  በጥንቃ እና በቁጠባ መጠቀም ይኖርብናል በተልይ የሕዝብ ቁጥር እየጨመረ ከተሞች እየሰፉ በመጡ ቁጥር  የውኃ አቅርቦትን ለማዳረስ ከውዲሁ ሊታሰብበት እና ልንሠራበት  ይገባል ያሉት ፕሮፌሰር ሰይፉ ከበደ  ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እራሳቸውን ያበቁ ባለሙያዎች ለማፍራት መስራት አለባቸው ብለዋል ። 

ሐና ደምሴ 

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሰ