1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሀዋሳ ሀይቅን ለመታደግ የሚደረግ ዘመቻ

ማክሰኞ፣ የካቲት 2 2013

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በደለል ሙላት የተነሳ ህልውናው በአደጋ ላይ የሚገኘውን የሀዋሳ ሀይቅ ለመታደግ ያስችላል ያለውን የአካባቢ ጥበቃ ዘመቻ በይፋ መጀመሩን አስታወቀ።

https://p.dw.com/p/3p7qe
See Hawassa I  Kampagne zum Umweltschutz
ምስል Shewangzaw Wegayehu/DW

የሀዋሳ ሀይቅን እንታደግ


የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር በደለል ሙላት የተነሳ ህልውናው በአደጋ ላይ የሚገኘውን የሀዋሳ ሀይቅ ለመታደግ ያስችላል ያለውን የአካባቢ ጥበቃ ዘመቻ በይፋ መጀመሩን አስታወቀ።
ለአንድ ወር ይቆያል በሚቆየው በዚሁ ዘመቻ በሀይቁ ዙሪያ በሚገኙ ቀበሌያት የአፈር መከላትን ለመከላከል የሚያስችሉ ሰራዎች እንደሚከናወኑ በዘመቻው ማስጀመሪያ ሰነ ስረዓት ላይ ተገልዷል ።
ዶቼ ቬለ (DW) ያነጋገራቸው የአካባቢ ጥበቃ ተቆርቋሪዎች በበኩላቸው መንግስት የተፈጥሮ ሀብት አንክብካቤን ከሰሞነኛ ዘመቻ ባለፈ የመደበኛ ስራው አካል ሊያደርግ ይገባል ብለዋል ።

See Hawassa I  Kampagne zum Umweltschutz
ምስል Shewangzaw Wegayehu/DW

ሸዋንዛው ወጋየሁ 
አዜብ ታደሰ 
ነጋሽ መሐመድ