1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዒድ አልፈጥር አከባበር በመቐለ

ዓርብ፣ ሚያዝያ 13 2015

የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ፕሬዝደንት ሓጂ መሓመድ አደም ያለፉት ሶስት ዓመታት የትግራይ ሙስሊም ማሕበረሰብ ፈታኝ ግዜ ያሳለፈበት እንደነበር ጠቅሰው፣ ይኽ ሁሉ አልፎ አሁን ላይ በተሻለ የበዓል ድባብ ረመዳን መፆሙ፥ በዓልም እየተከበረ መሆኑ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/4QPh4
Äthiopien Eid Al-Fitr in Mekelle
ምስል Million Haileselasie/DW

ዒድ አል ፈጠር በመቐለ

የዘንድሮ ዒድ ከጦርነቱ በኃላ በመቐለ በድምቀት ተከብሯል። ዛሬ በዓሉ ለማክበር በአስር ሺዎች ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በመቐለ በሚገኘው የሰማእታት ጎዳና በነበረ ስነስርዓት ከጦርነት ድባብ ውጪ ለመጀመሪያ ጊዜ ማክበራቸው ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረላቸው የበዓሉ ታዳሚዎች ለW ተናግረዋል። 

ዛሬ በመላው ዓለም በሙስሊሞች ዘንድ እየተከበረ ያለው 1444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል፣ ላለፉት ሁለት ዓመታት በጦርነት ላይ በነበረችው ትግራይም እንዲሁ በተሻለ የበዓል ድባር ሲዘከር ውሏል። በመቐለ በዓሉ ለማክበር ህዝበ ሙስሊሙ ወደ ሰማእታት ጎዳና መጉረፍ የጀመረው ከጠዋቱ 1 ሰዓት ጀምሮ ነው። በትግራይ የእስልምና ሃይማኖት መሪዎች፣ የእምነቱ መምህራን እንዲሁም በአስር ሺዎች የሚቋጠሩ ታዳሚያን በተገኙበት በዛሬው የዒድ በዓል ይፋዊ ስነስርዓት የክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር መሪዎችም ታድመውበታል።በዛሬው የበዓል መድረክ ለበዓሉ ታዳሚያን ንግግር ያሰሙት የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ፕሬዝደንት ሓጂ መሓመድ አደም ያለፉት ሶስት ዓመታት የትግራይ ሙስሊም ማሕበረሰብ ፈታኝ ግዜ ያሳለፈበት እንደነበር ጠቅሰው፣ ይኽ ሁሉ አልፎ አሁን ላይ በተሻለ የበዓል ድባብ  ረመዳን መፆሙ፥ በዓልም እየተከበረ መሆኑ ተናግረዋል። 

Äthiopien Mekelle Tigray | Öffentliches Fastenbrechen
ምስል Million Haileselassie/DW
Äthiopien Eid Al-Fitr in Mekelle
ምስል Million Haileselasie/DW

በዛሬው የመቐለ የዒድ አልፈጥር በዓል አከባበር ካለፉት ዓመታት እና በዓላት በርካታ ህዝብ የተገኘበት ሲሆን ያነጋገርናቸው ምእመናኑን የዘንድሮው ዒድ በደስታ፣ በሰላም፣ በተሻለ ሁኔታ እና መንፈስ እያከበሩት እንዳለ ገልፀውልናል።

ሚልዮን ሃይለስላሴ
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
እሸቴ በቀለ