1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ትምህርትአፍሪቃ

«የጥላቻ እና የፍቅር ቃላት» ድራማ

እሑድ፣ የካቲት 29 2012

ታሪኩ የሚከናወነው ለዓመታት ከዘለቀ አምባገነናዊ ሥርዓት፣ የጎሳ ክፍፍል እና ውጥረት በኋላ በአዲሱ ፕሬዝዳንት ካንዳ ዋ ባሩቲ አመራር ዴሞክራሲ ቀስ በቀስ ሥር ይሰድባት በጀመረው አፍሪካዊት አገር ማጋንጌ ነው።

https://p.dw.com/p/4YcDX
DW Crime Fighters Serienmotiv „Our tongue, our land“

በሀገሯ የጎሳ ግጭት እየጨመረ በመሄዱ አፍሪካዊቷ ወጣት ጋዜጠኛ ጁን የጥላቻ ንግግርን ለመዋጋት ወስናለች። ከአመታት የስደት ጉዞ በኋላ ፖለቲከኛ ባንኩ ወደ አገሯ ማጋንጌ ስትመለስ በተዘጋጀላት የአቀባበል ሥርዓት ላይ ድንገት በአደገኛ ሁኔታ በስለት ተወግታለች።  ይህ ደግሞ እሷ በምትወክለው ጎሳ እና  በስልጣን ላይ ባለው እና የኢኮኖሚውን የበላይነት በያዙት የጎሳ ግጭት እንደገና እንዲነሳ አድርጓል። የሁለቱም ጎሳዎች አባል የሆነችው ወጣት ጋዜጠኛ ጁን የጥላቻ ንግግሮችን እየታገለች ነው ። ይሳካላት ይሆን? ።  ለመሆኑ በባንኩ ላይ ጥቃቱን የፈጸሙት እነማን ናቸው? የደሬምባ ማህበረሰብ እንደሚለው ፕሬዝዳንቱ በእርግጥ በዚህ ተሳትፈዋልን? ኢንስፔክተር ኦፓንዴ ያገረሸው የጎሳ ግጭት ወደ እርስበርስ ጦርነት ከመሸጋገሩ በፊት ጉዳዩን ለመፍታት ከጊዜ ጋር ሩጫ ይዘዋል። 

 

ደራሲ: ክሪስፒን ምዋኪዲዮ

ትርጉም: እሸቴ በቀለ

ዝግጅት: ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ ዘገባዎች አሳይ