1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካየመካከለኛው ምሥራቅ

«በእሳት መካከል ነው ያለነው» ዜናነህ መኮንን

እሑድ፣ ሚያዝያ 6 2016

እስራኤል ከኢራን ለደረሰባት መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት ምን አይነት የአጸፋ ርምጃ እንደምትወስድ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም። «በእሳት መካከል ነው ያለነው» ሲል እየሩሳሌም የሚገኘው የመካከላኛው ምስራቅ የ DW ዘጋቢ ዜናነህ መኮንን ያለፉትን ሁለት ቀናት ይገልፃል።

https://p.dw.com/p/4ekDm
ቴላ ቪቭ  የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ስብሰባ ላይ
ከኢራን የአየር ጥቃት በኋላ የእስራኤል እና ዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ተቀምጠዋል። ምስል Israeli Prime Minister Office/AFP

ኢራን በእስራኤል ላይ ጥቃት ከዘሰዘረች በኋላ የዓለም አቀፋ አስተያየት

እስራኤል ከኢራን ለደረሰባት መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት ምን አይነት የአጸፋ ርምጃ እንደምትወስድ ለጊዜው የታወቀ ነገር የለም። ይሁንና ኢራን በበኩሏ እስራኤል ለደረሰባት ጥቃት የአጸፋ ርምጃ የምትወስድ ከሆነ የከፋ ርምጃ ልትወስድ እንደምትችል አስጠንቅቃለች።እስራኤል ለጋዛ ዕርዳታ እንዳይደርስ መከልከሏን እንድታቆም ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት አዘዘ

ይህም ህዝቡን ስጋት ላይ ጥሏል።  እስራኤል 99 በመቶ የተሰነዘረባትን ጥቃት ማክሸፍ ብትችልም ህዝቧ ከፍተኛ ድካም እና ጭንቀት ላይ ይገኛል። የእስራኤል ህዝብ አዳር ምን እንደሚመስል፤  እየሩሳሌም የሚገኘው የመካከላኛው ምስራቅ ዘጋቢያችን ዜናነህ መኮንን ሲገልፅ  «በእሳት መካከል ነው ያለነው» ሲል ነው። ስለ ደረሰው ጉዳት እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አስተያየት ተከታዩን ብሎናል። 
ዜናነህ መኮንን

ልደት አበበ