1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
እምነትአፍሪቃ

ኢድ አልፈጥር በሀዋሳ

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 2 2016

1 ሺህ 445 ኛው የኢድ አልፈጥር ክብረ በዓል በሀዋሳ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል ። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው የበዓሉ ተሳታፊዎች፦ በአገራችን ሰላም እንዲሰፍን ምእመኑ ፊቱን ወደ ፈጣሪ ሊያዞር ይገባል ብለዋል ።

https://p.dw.com/p/4ecnh
ሐዋሳ የሚሊኒየም አደባባይ የተሰባሰቡት የእምነቱ ተከታዮች ስግደት ላይ
ሐዋሳ የሚሊኒየም አደባባይ የተሰባሰቡት የእምነቱ ተከታዮች ስግደት ላይምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

የዒድ አል ፈጥር በዓል አከባበር በሐዋሳ

1 ሺህ 445 ኛው የኢድ አልፈጥር ክብረ በዓል በሀዋሳ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል ። ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው የበዓሉ ተሳታፊዎች፦ በኢትዮጵያ አገራችን ሰላም እንዲሰፍን ምእመኑ ፊቱን ወደ ፈጣሪ ሊያዞር ይገባል ብለዋል ።

1 ሺህ 445 ኛው የኢድ አልፈጥር ክብረ በዓል በሀዋሳ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል ፡፡ በተለይም ማለዳ በከተማው እምብርት በሚገኘው የሚሊኒየም አደባባይ የተሰባሰቡት የእምነቱ ተከታዮች ተኪቢራ አሰምተዋል ፤ የጁምኣ ሶላትም አከናውነዋል ፡፡

ዶቼ ቬለ ያነጋገራቸው የበዓሉ ተሳታፊዎች በአገራችን ሰላም እንዲሰፍን  ምእመኑ ፊቱን ወደ ፈጣሪ ሊያዞር ይገባል ብለዋል ፡፡ " የሰው ልጅ የተባለ በሙሉ ጸሎት ያሥፈልገዋል " ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ ” ያን ከፈጸመን ፈጣሪ ይሰማናል ፤ ሰላሙም ይመጣል " ብለዋል ፡፡

በበዓሉ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሲዳማ ክልል የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼህ አብዱልሻክር አብዱልቃድር በበኩላቸው ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ፈጣሪን በመያዝ በአንድ መንገድ እንዲጓዝ አሳስበዋል ፡፡

የረመዳን መጠናቀቅ አብሳሪ የሆነው ኢድ አልፈጥር ሙስሊሙ ማኅበረሰብ ለተቸገሩ  የምጽዋት እጆችን በመዘርጋትና ሃይማኖቱ የሚያዘውን በጐ ተግባር በመፈጸም እንደሚከበር ይታወቃል ፡፡

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሠ