1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ትግራይ ውስጥ ታፍነው የነበሩ የሠራዊት አባላት  

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 1 2013

በጥቅምት 24ቱ የመቀሌው ጥቃት ታፍነው ከነበሩ የመከላከያ ሠራዊት አባላት መካከል 5000 የሚሆኑት በጎንደር በኩል ወደ አማራ ክልል መግባታቸውን የክልሉ መንግሥት ባለስልጣናት አመለከቱ።

https://p.dw.com/p/3mXQo
Äthiopien Verteidigungstruppe Amhara
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

«በመንገዳችን ብዙ አጋጥሞናል»


በጥቅምት 24ቱ የመቀሌው ጥቃት ታፍነው ከነበሩ የመከላከያ ሠራዊት አባላት መካከል 5000 የሚሆኑት በጎንደር በኩል ወደ አማራ ክልል መግባታቸውን የክልሉ መንግሥት ባለስልጣናት አመለከቱ። የሠራዊቱ አባላት በመንገድ ብዙ ውጣውረድ ማሳለፋቸውን ይናገራሉ። ትግራይ ክልል በቆዩበት በዚህ ወቅት  ስንቅ ሰጥተው የሸኟቸው እንዳሉ ሁሉ፣ በተቃራኒው ከትግራይ ልዩ ኃይል አባላት የዘረፏቸው እንዳሉ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል። የመከላከያ ሠራዊቱ አባላት የገቡበት በሰሜን ጎንደር የበየዳ ወራዳ ሕዝብ ለእነሱ አስፈላጊውን ሁሉ እገዛ ማድረጉም ተሰምቷል። 


ዓለምነው መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ