1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጋምቤላ ክልል አራት አመራር ከኃላፊነታቸው ተነሱ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 1 2016

የጋምቤላ ክልል መንግስት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም ያላቸውን 4 አመራር ከስልጣን ማንሳቱን አስታወቀ፡፡ አመራር ከስልጣናቸው የተነሱት ከጸጥታ ችግር ጋር ተያይዞ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በአግባቡ ባለመፈጸማቸው እንደሆነ የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽፈት ቤት አመልክቷል፡፡

https://p.dw.com/p/4eZwx
Äthiopien | Straßenszene in Gambela
ምስል Negassa Desalegn/DW

የጋምቤላ ክልል መንግስት 4 ባለስልጣናት ከኃላፊነት አነሳ

የጋምቤላ ክልል መንግስት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም ያላቸውን 4 አመራር ከስልጣን ማንሳቱን አስታወቀ፡፡ አመራር ከስልጣናቸው የተነሱት ከጸጥታ ችግር ጋር ተያይዞ የተሰጣቸውን ተልዕኮ በአግባቡ ባለመፈጸማቸው እንደሆነ የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽፈት ቤት አመልክቷል፡፡ ከስልጣናቸው የተነሱት የክልሉ የሠላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አቶ ቾል ኩን፣ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ አኳይ አቡቲ፣ የኑዌር ብሔረሰብ ዞን ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቡኝ ኒያል እና የክልሉ ገጠር መንገዶች ባለስልጣን ኃላፊ አቶ ቢተው ዳክ ናቸው፡፡ በክልሉ በተከሰተው  የጸጥታ ችግር ውስጥ እጃቸው አለበት ተብሎ የተጠረጠሩ አካላትን በመለየት እርምጃ እንደሚወስድ የክልሉ መንግስት ገልጸዋል፡፡

በጋምቤላ ክልል ተከስቶ የነበሩ ግጭቶችን ለማስቆም በወንጀል ድርጊት ተሳትፈዋል ተብሎ የተጠረጠሩ ግለሰቦችነ በቁጥጥር ስር ከማዋል ጀምሮ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ልዩ ልዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን ማወያየቱን የክልሉ መንግስት አመልክቷል፡፡ የክልሉ መንግስት ከጸጥታ ችግር ጋር ተያይዞ ኃላፊነታቸውን አልተወጡም ያላቸውን አራት አመራር ከኃላፊነት ማንሳቱን ገልጿል፡፡ ከኃላፊነታቸው ከተነሱት መካካል አንዱ በሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም የክልሉ ሠላም እና ጸጥታ አስተዳደር ኃላፊ ሆነው የተሾሙት አቶ ቾል ኩን ናቸው፡፡

በጋምቤላ ክልል በላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች መበራከት

በክልሉ በጸጥታ ችግር አሁንም የሰው ሕይወት እያለፈ ይገኛል

የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኡጁሉ ጊሎ በሰጡን ማብራሪያ ከኃላፊነታቸው የተነሱት አመራር የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ ባለመወጣታቸውና ውጤታማ ባለመሆናቸው ነው ብሏል፡፡

የጋምቤላ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳድር
በጋምቤላ ክልል ተከስቶ የነበሩ ግጭቶችን ለማስቆም በወንጀል ድርጊት ተሳትፈዋል ተብሎ የተጠረጠሩ ግለሰቦችነ በቁጥጥር ስር ከማዋል ጀምሮ በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ልዩ ልዩ የማህበረሰብ ክፍሎችን ማወያየቱን የክልሉ መንግስት አመልክተዋል፡፡ ምስል Gambella Communication

ክልሉ ጠረፋማ አካባቢ ከመሆኑም የተነሳ ድምበር ዘለል የታጣቂ ቡድኖች እንቅስቃሴ በተደጋጋሚ በክልሉ ውስጥ እንደሚተዋልም ተገልጸዋል፡፡ የክልሉ መንግስት ከዚህ ቀደም ባወጣው መግለጫም በአካባቢው ለሚስተዋለው ጸጥታ ችግር በዋናነት አመራሮችን ተጠያቂ አድርጓል፡፡ በተጨማሪም ኢ-መደበኛ ያላቸው አደረጃጀቶችም በክልሉ የተከሰቱ ግጭቶች ውስጥ ተሳታፊ መሆናቸውን አክለዋል።

ጋምቤላ ዉስጥ ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት ሰዎች ገደሉ

ያነጋገርናቸው የጋምቤላ ከተማ ነዋሪዎች በበኩላቸው በክልሉ ተከስቶ የነበሩ የጸጥታ ችግሮችን  አመራሩ ባለስማቆሙና በማባበሱ ተጠያቂ መሆን አለበባቸው ሲሉ አስተያየት ሰጥቷል፡፡ ኃላፊነታቸውን አልተወሰጡም ተብለው ከስልጣናቸው ተነሱ የተባሉ አመራሮችም በህግ ተጠያቂ መሆን አለባቸው ብሏል፡፡

በጋምቤላ ክልል ለተራዘሙ ጊዜ በቆየው የጸጥታ ችግር ጋር ተያየዞ በነሐሴ ወር መጨረሻ 2015 ዓ.ም እንደዚሁ 13 አመራሮች ከኃላፊነታቸው መነሳታቸውን የክልሉ መንግስት በወቅቱ ገልጸዋል፡፡ በወቅቱ በክልሉ የተወሰኑ አካባቢዎች ተከስቶ በነበረው የጸጥታ ችግር ምክንያት በተደረገው ግምገማ አመራሩን ከኃላፊነታቸው ማንሳቱን የክልሉ መንግስት አመልክተዋል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

ታምራት ዲንሳ 

ሸዋዬ ለገሰ